1 ነፈርሆተፕ
==
ነፈርሆተፕ ኻሰኸምሬ | |
---|---|
የነፈርሆተፕ ምስል | |
የግብጽ ፈርዖን | |
ግዛት | 1701-1690 ዓክልበ. ግ. |
ቀዳሚ | 3 ሶበክሆተፕ |
ተከታይ | ካነፈሬ 4 ሶበክሆተፕ |
ባለቤት | ሰነብሰን |
ሥርወ-መንግሥት | 13ኛው ሥርወ መንግሥት |
አባት | ሀዓንኸፍ |
==
1 ነፈርሆተፕ ኻሰኸምሬ ግብጽ በ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ከ1701 እስከ 1690 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ። የ3 ሶበክሆተፕ ተከታይ ነበረ።
በቶሪኖ ቀኖና ዘንድ ኻሰኸምሬ ነፈርሆተፕ ለ፲፩ ዓመት ገዛ ሲለን ለእርሱ ብዙ ሐውልቶችና ቅርሶች ይታወቃሉ። እንደ ቀዳሚው ፫ ሶበክሆተፕ ከወታደራዊ ቤተሠብ እንደ መጣ ይመስላል። አባቱ ሀዓንኸፍና እናቱ ከሚ ነበሩ፤ የዚህም ሀዓንኸፍ አባት ነሂ እናቱም ሰነብቲሲ ተባሉ። ይህም ነሂ «የከተማ ሻለቃ» የሚመስል ማዕረግ እንደ ነበረው ይታወቃል። የሀዓንኸፍ ፫ ልጆች ሁሉም ፈርዖኖች ስለ ሆኑ በበርካታ ጽላቶች ይከበራል። የነፈርሆተፕ ልጆች ደግሞ ልዑል ሀዓንኸፍና ልዕልት ከሚ ተባሉ።
በጌባል (በፊንቄ) የተገኙት ቅርሶች የነፈርሆተፕ «አገረ ገዥ» በጌባል «ያንቲኑ» እንደ ነበር ያስረዳሉ። እሱም ከማሪ ጽላቶች ያንቲን-ዓሙ «የጌባል ንጉሥ» ይባላል። ይህም ነፈርሆተፕ በባቢሎን ንጉሥ ሃሙራቢ ዘመን እንደ ነገሠ ማስረጃ ነው።
ወደ ነፈርሆተፕ ዘመን መጨረሻ ወንድሙ ሲሐጦር ከእርሱ ጋራ የጋርዮሽ ፈርዖን ተደርጎ ሲሐጦር በጥቂት ወራት ውስጥ እንደ ሞተ ይመስላል፤ ከዚያም ሌላ ወንድማቸው ካነፈሬ 4 ሶበክሆተፕ የጋርዮሽ ፈርዖን ሆነ። ከዚያም ትንሽ በኋላ ነፈርሆተፕ ዓርፎ ካነፍሬ ሶበክሆተፕ ለብቻ ፈርዖን ሆነ።
ቀዳሚው 3 ሶበክሆተፕ |
የግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን | ተከታይ ካነፈሬ 4 ሶበክሆተፕ |
ዋቢ ምንጭ
ለማስተካከል- K.S.B. Ryholt: The Political Situation in Egypt during the Second Intermediate Period, c. 1800 – 1550 BC, Carsten Niebuhr Institute Publications, vol. 20. Copenhagen: Museum Tusculanum Press, 1997 (እንግሊዝኛ)