ሰነፈሪብሬ 4 ሰኑስረትላይኛ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን (16ኛው ሥርወ መንግሥት) ምናልባት 1592 ዓክልበ. አካባቢ የገዛ ፈርዖን ነበረ።

ሰኑስረት 4 ሰነፈሪብሬ
የሰኑስረት ሰነፈሪብሬ ሐውልት
የሰኑስረት ሰነፈሪብሬ ሐውልት
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1592 ዓክልበ. ግ.
ቀዳሚ መራንኽሬ 6 መንቱሆተፕ ?
ተከታይ 2 ደዱሞስ
ሥርወ-መንግሥት 16ኛው ሥርወ መንግሥት

ስሙ የሚታወቅ ከአንድ ትልቅ ሐውልት፣ በ1ኛው ዓመት ከተቀረጸ ጽላትና ከአንዳንድ ጥቃቅን ቅርሶች ነው። ከዚህ በላይ በካርናክ ዝርዝር ላይ «ሰነፈር<...>ሬ» የተባለ ፈርዖን ይገኛል።

ቶሪኖ ቀኖና ዝርዝር ላይ ከሰኸምሬ ሸድዋሰት ቀጥሎ አምስት የፈርዖን ስሞች ጠፍተዋል። በአቶ ኪም ራይሆልት አስተሳሰብ ሰነፈሪብሬ በነዚህ አምስት መካከል ነበሩ።


ቀዳሚው
መራንኽሬ 6 መንቱሆተፕ
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን
1592 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
2 ደዱሞስ