ረንሰነብ አመነምሃት (ወይም ራኒሶንብ) ላይኛ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) በ1791 ዓክልበ. ግድም የገዛ ፈርዖን ነበረ። የኻአንኽሬ ሶበክሆተፕ ተከታይ ነበረ።

ረንሰነብ አመንሆተፕ
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1791 ዓክልበ. ግ.
ቀዳሚ ኻአንኽሬ ሶበክሆተፕ
ተከታይ ሆር አዊብሬ
ሥርወ-መንግሥት 13ኛው ሥርወ መንግሥት
አባት አመነምሃት ?

ስሙ በቶሪኖ ቀኖና ነገሥታት ዝርዝር ሲገኝ ዘመኑ ለ፬ ወር ብቻ እንደ ቆየ ይላል። አንድ ቅርስ ብቻ እሱም «ረንሰነብ አመነምሃት» የሚል ዶቃ ሕልውናውንና ሁለተኛውን ስም አመነምሃት ያሳያል። በአቶ ራይሆልት አሳብ፣ ይህ ማለት የአመነምሃት (፭፣ ፮፣ ፯?) ልጅ እንደ ነበር ያስያል።

ቀዳሚው
ኻአንኽሬ ሶበክሆተፕ
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን
1791 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሆር አዊብሬ

ዋቢ ምንጭ ለማስተካከል

  • K.S.B. Ryholt: The Political Situation in Egypt during the Second Intermediate Period, c. 1800 – 1550 BC, Carsten Niebuhr Institute Publications, vol. 20. Copenhagen: Museum Tusculanum Press, 1997 (እንግሊዝኛ)