ዋህካሬ ቀቲ
ዋህካሬ ቀቲ ከ2417 እስከ 2350 ዓክልበ. ግድም ድረስ የግብፅ 9ኛው ሥርወ መንግሥት መጀመርያው ፈርዖን ነበረ። የዋህካሬ ቀቲ ሕልውና የሚታወቅ ከአንድ የሬሳ ሣጥን ጽሑፍ ብቻ ነው። ይህ ጽሑፍ ግን በ1930 ዓክልበ. (በ12ኛው ሥርወ መንግሥት ዘመን) እንደ ተጻፈ ስለሚመስል፣ ሊቃውንቱ በኋለኛ ዘመን የተጻፈ ቅጂ መሆኑን ያስባሉ። ይህ ጽሑፍ ይዞታ በተለይ ከድሮው ጥንታዊ መንግሥት የሀረም ጽሕፈቶች የተወሰደ ነው። ስለ ዋህካሬ ጥቂት አዲስ መረጃ ብቻ አለበት፤ ለምሳሌ «ዋህካሬ ሆይ፣ ንቃ! ሔሩ ጠላትህን በፊትህ በትኗል፤ ከጠላትህ ይልቅ ዕድሜ አለህ፤ ከርሱም በፊት መጣህ» ይላል። ስለዚህ የጥንታዊ መንግሥት አረመኔ ሃይማኖት በመካከለኛው ዘመን እንደተመለሰ ማለት ይቻላል።
አንዳንድ የአሁን ሊቃውንት ከአንድ «ዋህካሬ ቀቲ» በላይ እንደ ገዛ ይላል፤ ለምሳሌ ዊልያም ዋርድ እንደ መሰለው፣ 2 ወይም 3 ዋህካሬ ቀቲ የመሪካሬ አባትና የመሪካሬ ትምህርት ደራሲ መሆኑን ያስባል። ዳሩ ግን ለዚሁ ሀሣብ ምንም ማስረጃ የለም።
ቀዳሚው (አይታወቅም) |
የግብፅ ፈርዖን | ተከታይ ቀቲ (አቅቶይ) |