መርነፈሬ አይ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ምናልባት ከ1665 እስከ 1661 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ።

መርነፈሬ አይ
የመርነፈሬ ቅርስ
የመርነፈሬ ቅርስ
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1665-1661 ዓክልበ. ግ.
ቀዳሚ ዋሂብሬ ኢቢያው
ተከታይ መርሆተፕሬ ኢኒ
ሥርወ-መንግሥት 13ኛው ሥርወ መንግሥት

የቶሪኖ ቀኖና በተባለው ዝርዝር ዘንድ፣ ዘመኑ ለ፳፫ ዓመታትና ፰ ወር ቆየ፤ ዳሩ ግን ለዘመኑ ቅርሶቹ ወይም ፍርስራሶቹ ጥቂት በመሆናቸው እስከዚያ ያህል ድረስ መግዛቱ አጠራጣሪ ነው። የግብጽ ታሪክ መምህሮች እንደሚያውቁ በዘመኑ መጨረሻ «አስተዳደሩ ፈጽሞ ወድቆ ነበር ይመስላል»። ዋና ከተማው እጅታዊ ከርሱ በኋላ ተተወ፣ ተከታዮቹም የጤቤስ ገዦች ብቻ እንጂ የመላውን ግብጽ ፈርዖኖች አልነበሩም። የዚህ ምክንያት የግብጽ ሃይል እጅግ ተደክሞ ሂክሶስ የተባለው አሞራዊ ወገን በዚያን ጊዜ በስሜን ወረራ ስላደረገ ነው።

የመርነፈሬ አይ መቃብር እስካሁን መቸም አልተገኘም።

ቀዳሚው
ዋሂብሬ ኢቢያው
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን
1665-1661 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
መርሆተፕሬ ኢኒ

ዋቢ ምንጭ ለማስተካከል

  • K.S.B. Ryholt: The Political Situation in Egypt during the Second Intermediate Period, c. 1800 – 1550 BC, Carsten Niebuhr Institute Publications, vol. 20. Copenhagen: Museum Tusculanum Press, 1997 (እንግሊዝኛ)