ዋጅካሬ የግብጽ የቀድሞ ዘመነ መንግሥት 8ኛው ሥርወ መንግሥት ፈርዖን ነበረ።

በ7ኛውና 8ኛው ሥርወ መንግሥታት ከተዘረዘሩት ፈርዖኖች ለብዙዎቹ ምንም ፍለጋ ወይም ቅርስ ስላልተገኘ፣ መቸም በእውነት እንደ ነገሡ አይታሥብም። ለዋጅካሬ ዘመን ግን አንድ ጽላት ሰነድ (የቆጵቶስ አዋጆች 'R') ይታወቃል። ይህ ሰነድ የመንግሥትን ነዋይ ለሚያጎዱ ሁሉ ቅጣቱን የሚወስን አዋጅ ነው። በሰነዱ መጨረሻ «ዋጅካሬ፣ የሐብ ልጅ» ሲል፣ በመቅደሙ «ሔሩ ደመጂብታዊ» ይላል፤ ይህ የዋጅካሬ ሌላ ስም እንደ ሆነ በብዙ ይታስባል። ሰነዱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢዲ (የሸማይ ልጅ) ይጻፋል። ሸማይ የቀድሚው የነፈርካውሆር ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ ነበር።

ዋጅካሬ በግብጽ ቀድሞ ዘመን መንግሥት መጨረሻ (2764-2763 ዓክልበ. ግድም) የነገሠው ፈርዖን ይመስላል። በአቢዶስ ፈርዖኖች ዝርዝር ላይ መጨረሻው ፈርዖን «ነፈሪርካሬ» ይባላል። በሸማይ መቃብር ውስጥ፣ አንድ ጽላት ከፈርዖኑ «ፐፒ ነፈሪርካሬ ተገኝቶ ለሸማይ ልጅ ኢዲ እንደ ተጻፈ ይታስባል። ስለዚህ «ፐፒ ነፈሪርካሬ»፣ «ሔሩ ደመጂብታዊ» እና «ዋጅካሬ» ሁሉ የመጨረሻ ፈርዖን ስሞች እንደ ነበሩ ሊሆኑ ይቻላል።

ቶሪኖ ቀኖና ላይ በመጨረሻው ቦታ ስሙ ጠፍቷል፣ ፈርዖኑ ግን ለ1 ዓመት ተኩል እንደ ገዛ ይላል።

የውጭ መያያዣ

ለማስተካከል