==

ሳንኸንሬ መንቱሆተፒ
«ሳንኸንሬ» የሚል እስፊንክስ ቅርስ
«ሳንኸንሬ» የሚል እስፊንክስ ቅርስ
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1636-35 ዓክልበ. ግ.
ቀዳሚ 3 ነፈርሆተፕ
ተከታይ 1 ነቢሪራው
ሥርወ-መንግሥት 16ኛው ሥርወ መንግሥት

==


ሳንኸንሬ መንቱሆተፒ (ወይም «7 መንቱሆተፕ») በላይኛ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን (16ኛው ሥርወ መንግሥት) ምናልባት 1636-1635 ዓክልበ. አካባቢ የገዛ ፈርዖን ነበረ።

ስሙ «ሳንኸንሬ መንቱሆተፒ» የሚታወቀው ከአንዳንድ ቅርስ ነው።

  • ካርናክ የተገኘ ጽላት «የጤቤስ ንጉስ» እንደ ተባለ ከሂክሶስም ጋር እንደ ተዋጋ ይገልጻል።
  • «ሳንኸንሬ» በሚል በአንድ ጥንዚዛ ቅርጽ
  • ሁለት እስፊንክስ ምስሎች በኤድፉ በ1916 ዓም ተገኙ፣ አንዱ «ሳንኸንሬ» ሲል ሌላው «መንቱሆተፒ» ይላል።
  • ቶሪኖ ቀኖና ዝርዝር ላይ «ሰ...ኧንሬ» ለ1 ዓመት እንደ ገዛ ይላል። ሙሉ ስም አሁን ሊነብብ አይቻልም።
ቀዳሚው
3 ነፈርሆተፕ
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን
1636-1635 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
1 ነቢሪራው