==

ጀድሆተፕሬ ደዱሞስ
የጀድሆተፕሬ ደዱሞስ ጽላት
የጀድሆተፕሬ ደዱሞስ ጽላት
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1595 ዓክልበ. ግ.
ቀዳሚ ሰኸምሬ ሸድዋሰት ?
ተከታይ ሞንተምሳፍ
ሥርወ-መንግሥት 16ኛው ሥርወ መንግሥት

==


ጀድሆተፕሬ ደዱሞስላይኛ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን (16ኛው ሥርወ መንግሥት) ምናልባት 1595 ዓክልበ. አካባቢ የገዛ ፈርዖን ነበረ።

ስሙ «ጀድሆተፕሬ ደዱሞስ» ከአንድ ጽላት ይታወቃል። ከእርሱ በኋላ ጀድነፈርሬ 2 ደዱሞስ አለ። አንዳንድ ሌላ ቅርስ ወይም ጽላት «ደዱሞስ» ሲል የትኛው ደዱሞስ እንደ ሆነ እርግጥኛ አይደለም።

ቶሪኖ ቀኖና ዝርዝር ላይ ከሰኸምሬ ሸድዋሰት ቀጥሎ አምስት የፈርዖን ስሞች ጠፍተዋል። በአቶ ኪም ራይሆልት አስተሳሰብ ደዱሞስ 1 እና 2 በነዚህ አምስት መካከል ነበሩ።

ቀዳሚው
ሰኸምሬ ሸድዋሰት
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን
1595 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሞንተምሳፍ