ኹታዊሬ ወጋፍ
==
ኹታዊሬ ወጋፍ | |
---|---|
የ«ኹታዊሬ ወጋፍ» ስም ያለበት ቅርስ | |
የግብጽ ፈርዖን | |
ግዛት | 1776-1774 ዓክልበ. ግ. |
ቀዳሚ | ሰጀፋካሬ |
ተከታይ | ኡሰርካሬ ኸንጀር |
ሥርወ-መንግሥት | 13ኛው ሥርወ መንግሥት |
==
ኹታዊሬ ወጋፍ (ወይም ኡጋፍ) ላይኛ ግብጽ በ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ከ1776 እስከ 1774 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ። ምናልባት የሰጀፋካሬ ተከታይ ነበረ።
በቶሪኖ ቀኖና ነገሥታት ዝርዝር ላይ «ኹታዊሬ» በ፲፫ኛው ሥርወ መንግሥት መጀመርያው ይገኛል። በመምኅር ኪም ራይሆልት አስተሳሰብ፣ ይህ ለ«ኹታዊ» (ሰኸምሬ ኹታዊ 1 ሶበክሆተፕ) በዝርዝሩ ላይ ተሳተ፤ ኹታዊሬም በሶበክሆተፕ ፈንታ በ፲፱ኛው ሥፍራ ከኡሰርካሬ ኸንጀር አስቀድሞ እንደ ገዛ ይመስለዋል። ከሥነ ቅርስ ረገድ ደግሞ ፈርዖንነቱ እርግጥኛ ነው።
ቀዳሚው ሰጀፋካሬ |
የግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን | ተከታይ ኡሰርካሬ ኸንጀር |
ዋቢ ምንጭ
ለማስተካከል- K.S.B. Ryholt: The Political Situation in Egypt during the Second Intermediate Period, c. 1800 – 1550 BC, Carsten Niebuhr Institute Publications, vol. 20. Copenhagen: Museum Tusculanum Press, 1997 (እንግሊዝኛ)