አፐፒጥንታዊ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን15ኛው ሥርወ መንግሥት (ሂክሶስ) ፈርዖን ነበር።

አፐፒ
አፐፒ የሚል ጥንዚዛ
አፐፒ የሚል ጥንዚዛ
የግብጽ (ሂክሶስ) ፈርዖን
ግዛት 1593-1560 ዓክልበ. ግ. ?
ቀዳሚ ሻሙቄኑ
ተከታይ ኻሙዲ
ሥርወ-መንግሥት 15ኛው ሥርወ መንግሥት
«ነብኸፐሽሬ አፐፒ» የሚል ጩቤ

ስሙና ሕልውናው ከበርካታ ቅርሶች ይታወቃል። ሦስት የዙፋን ስሞች ነበሩዋቸው፦ ነብኸፐሽሬ (1593-1577 ዓክልበ. ግድም)፣ አቀነንሬ (1577-1570 ዓክልበ. ግድም) እና አውሰሬ (1570-1560 ዓክልበ.) ነበሩ።

አፐፒ ለጥቂት ጊዜ 1590-1588 ዓክልበ. እስከ ጤቤስ ድረስ እንዳሸነፈ ይታሥባል። ከዚያ በኋላ አዲሱ 17ኛው ሥርወ መንግሥት በጤቤስ ተነሣ።

በኋላ በ1200 ዓክልበ. ገደማ በተጻፉ መዝገቦች ዘንድ፣ የዚህ አፐፒ አምላክ ሴት ብቻ ነበር እንጂ ሌላ ጣኦት አላመለከም። ሆኖም የሄሩ (ሰረኽ) ስም ሰሖተፕታዊ እንደ ነበረው ይታወቃል።

አፐፒ ደግሞ የቀድሞ ፈርዖኖች የ2 አመነምሃት (1938-1905 ዓክልበ. ገ.) እና የስመንኽካሬ ኢሚረመሻው (1766-1754) ሐውልቶች ሠርቆ በስማቸው ላይ የራሱን ካርቱሽና «ለአቫሪስ ጌታ ለሴት (ጣኦቱ) ክብር» ብሎ ቀረጸና ሥፍራቸውን ወደ አቫሪስ አዛወራቸው።

በተለያዩ ቅርሶች መሠረት ወንድ ልጅ «ልዑል አፐፒ»፣ ሴት ልጅ «ሄሪት»፣ እኅት «ታኒ» እንደ ነበሩት ይታወቃል። የሌላውም እኅት የ«ዚዋት» ዕቃ በእስፓንያ ተገኝቷል።

ማኔቶን ልዩ ልዩ ቅጂዎች ስሞቹ ከግሪክኛ ተዛብተዋል፣ «አፖፊስ»፣ «አፎፊስ» ወይም «አፎቢስ» ይባላል፤ 61 ወይም በአውሳብዮስ ቅጂ 14 ዓመታት ይሰጡታል። በቶሪኖ ቀኖና ዝርዝር ላይ በሥፍራው ያለው ስም ባይተርፍም ዘመኑ 40 ዓመት እንደሚል ይታስባል። የራይንድ ሥነ ቁጥራዊ ፓፒሩስ የተባለው ሰነድ በአፐፒ (አውሰሬ) 33ኛው ዓመት እንደ ተቀነባበረ ይላል። በዚህም ዓመት ያሕል የጤቤስ ፈርዖን ካሞስ ፫ኛው ዓመት ሲሆን፣ ካሞስ የአፐፒን ሥራዊት አሸንፎ ጠረፉን ከአቫሪስ 100 ማይል እስካለው ድረስ እንዳሰፋው በሌላ ጽላት ተገኝቷል። ይህ ወደ አፐፒ ዘመን መጨረሻ ሆነ፣ መጨረሻውም ሂክሶስ ፈርዖን ኻሙዲ በአቫሪስ እንደ ተከተለው ይታመናል።


ቀዳሚው
ሻሙቄኑ
ግብፅ (ሂክሶስ) ፈርዖን
1593-1560 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ኻሙዲ