1 ሶበከምሳፍ
==
ሰኸምሬዋጅኻው ሶበከምሳፍ | |
---|---|
የ1 ሶበከምሳፍ ሐውልት | |
የግብጽ ፈርዖን | |
ግዛት | 1584-1577 ዓክልበ. ግ. |
ቀዳሚ | ራሆተፕ ? |
ተከታይ | 2 ሶበከምሳፍ |
ባለቤት | ኑበምሃት |
ሥርወ-መንግሥት | 17ኛው ሥርወ መንግሥት |
==
ሰኸምሬዋጅኻው ሶበከምሳፍ በላይኛ ግብጽ በ2ኛው ጨለማ ዘመን (17ኛው ሥርወ መንግሥት) ምናልባት 1584-1577 ዓክልበ. አካባቢ የገዛ ፈርዖን ነበረ።
ስሙ የሚታወቅ በተለያዩ ጽላቶችና ሐውልቶች ነው። ጉዞዎች ወደ ዋዲ ሐመመት ድንጋይ መፍለጫ ይላክ እንደ ነበር ይታወቃል። አንዱ ጽሑፍ ከ7ኛው አመት ሲሆን ዘመኑ ቢያንስ 7 ዓመት እንደ ቀረ ሊታወቅ ይችላል። እንዲሁም ንግሥቱ ኑበምሃት፣ ሴት ልጁ ሶበከምኸብ፣ እና ወንድ ልጁ ተከታዩ 2 ሶበከምሳፍ ይታወቃሉ።
ቀዳሚው ራሆተፕ |
የግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን 1584-1577 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ 2 ሶበከምሳፍ |