==

ሳኪር-ሃር
የግብጽ (ሂክሶስ) ፈርዖን
ግዛት 1661-1642 ዓክልበ. ግ. ?
ቀዳሚ መርነፈሬ አይ
ተከታይ አፐር-አናቲ
ሥርወ-መንግሥት 15ኛው ሥርወ መንግሥት

==


ሳኪር-ሃርጥንታዊ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን15ኛው ሥርወ መንግሥት (ሂክሶስ) ፈርዖን ነበር። ስሙ ወይም ሕልውናው መጀመርያው በ1990 ዓም ያህል በስነ ቅርስ ተገኘ፤ ይህም «የሂክሶስ ፈርዖን ሳኪር-ሃር» በሚል ደጃፍ መቃን ላይ ነው። ከመጀመርያ ሦስቱ የሂክሶስ ፈርዖኖች አንዱ እንደ ሆነ ይታሥባል፣ የትኛው እንደ ሆነ ግን እርግጥኛ አይደለም።

ማኔቶን ልማድና በተለይ በዮሴፉስ (71 ዓም) እንደ ተገለጸ፣ የሂክሶስ መጀመርያ ንጉሥ «ሳሊቲስ» (ወይም «ሳይቴስ፣ ሳላቲስ») ሲባል፣ ሂክሶስም ከእስያ በፈርዖን «ቱቲማዮስ» ወይም «ቲማዮስ» ዘመን ወርረው ታችኛ (ስሜን) ግብጽ ያዙ፤ ሳሊቲስ በሜምፊስ ይቀመጥ ነበር፣ አቫሪስ ከተማ ግን እንደ አምባ አድርጎ በዚያ የጦርነት ሠልፍ አስተማረ። ከ19 ዓመታት በኋላ ሌላ ሂክሶስ ሰው «ብኖን» ተከተለው። እነዚህ ስሞች በዘመናት ላይ ከግብጽኛቅብጥኛግሪክኛና በሌሎች ልሳናት በኩል በመተረጎማቸው ቢዛቡም፣ ይህ መጀመርያ ሂክሶስ አለቃ «ሳሊቲስ» እና «ሳኪር-ሃር» አንድ ሊሆኑ ይቻላል። ስለዚህ በግምት ዘመኑ ምናልባት 1661-1642 ዓክልበ. ያህል ሊገኝ ይቻላል።

ቀዳሚው
መርነፈሬ አይ
ግብፅ (ሂክሶስ) ፈርዖን
1661-1642 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
አፐር-አናቲ

ዋቢ ምንጭ

ለማስተካከል
  • K.S.B. Ryholt: The Political Situation in Egypt during the Second Intermediate Period, c. 1800 – 1550 BC, Carsten Niebuhr Institute Publications, vol. 20. Copenhagen: Museum Tusculanum Press, 1997 (እንግሊዝኛ)