ስመንኽካሬ ኢሚረመሻው
==
ስመንኽካሬ ኢሚረመሻው | |
---|---|
የኢሚረመሻው ሐውልት በ1889 ዓ.ም. ሲገኝ | |
የግብጽ ፈርዖን | |
ግዛት | 1766-1754 ዓክልበ. ግ. |
ቀዳሚ | ኡሰርካሬ ኸንጀር |
ተከታይ | ሰኸተፕካሬ አንተፍ |
ሥርወ-መንግሥት | 13ኛው ሥርወ መንግሥት |
==
ስመንኽካሬ ኢሚረመሻው ላይኛ ግብጽ በ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ከ1766 እስከ 1754 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ። የኡሰርካሬ ኸንጀር ተከታይ ነበረ።
በቶሪኖ ቀኖና ነገሥታት ዝርዝር ላይ «<..>ካሬ ኢሚረመሻው» ይገኛል። ከተገኙት ሁለት ታላቅ ሐውልቶች በቀር ስሙ በአንድ ዶቃ ላይ ተቀርጾ ተግኝቷል።
በዚህ ዘመን «ኦሩስ፣ አኸንኸሬስ፣ አኮሪስ፣ ኸንክሬስ፣ አክኸሬስ» በግብጽ እንደ ገዙ በአንዳንድ ምንጭ ይገኛል። እነዚህ ስሞች ሆር አዊብሬ፣ ሰኸምሬኹታዊ ኻውባው፣ ሰጀፋካሬ፣ ኡሰርካሬ ኸንጀር፣ እና ስመንኽካሬ ቢመስሉም፣ ከማኔጦን ጀምሮ ስሞቻቸው ከ፲፱ኛው ሥርወ መንግሥት ፈርዖኖች ጋር እንደ ተዛቡ ይመስላል። «አክኸሬስ» የ፲፪ ዓመታት ዘመን እንደ ነበረው ይባላል። በመምኅር ኪም ራይሆልት ግመት ስመንኽካሬ ለ5-10 ዓመታት ብቻ ገዛ፤ ማስረጃ ግን የለም።
ቀዳሚው ኡሰርካሬ ኸንጀር |
የግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን | ተከታይ ሰኸተፕካሬ አንተፍ |
ዋቢ ምንጭ
ለማስተካከል- K.S.B. Ryholt: The Political Situation in Egypt during the Second Intermediate Period, c. 1800 – 1550 BC, Carsten Niebuhr Institute Publications, vol. 20. Copenhagen: Museum Tusculanum Press, 1997 (እንግሊዝኛ)