3 አመነምሃት
==
3 አመነምሃት | |
---|---|
የኒመዓትሬ ምስል | |
የግብጽ ፈርዖን | |
ግዛት | 1859-1832 ዓክልበ. |
ቀዳሚ | 3 ሰኑስረት |
ተከታይ | 4 አመነምሃት |
ሥርወ-መንግሥት | 12ኛው ሥርወ መንግሥት |
አባት | 3 ሰኑስረት |
==
ኒመዓትሬ፣ ፫ አመነምሃት ግብጽን በመካከለኛ መንግሥት (12ኛው ሥርወ መንግሥት) ከ1859 እስከ 1832 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ። የአባቱ 3 ሰኑስረት ተከታይ ነበር።
በኻኻውሬ 3 ሰኑስረት ዘመነ መንግሥት በ1879 ዓክልበ. ግድም ልጁን ፫ አመነምሃት ከእርሱ ጋር በጋርዮሽ ወደ ዙፋኑ አስነሣው። ስለዚህ የ፫ አመነምሃት ዘመን መጀመርያ ዓመት የሚቆጠር ከ1879 ዓክልበ. ግድም ይሆናል። በጠቅላላ ለ47 ዓመታት ያህል እንደ ገዛ ይታወቃል።
አንድ ሀረም «ጥቁሩ ሀረም» ጀምሮ ነበር ግን አሠራሩ ተቸግሮ አልጨረሰውም፤ ሌላ ታላቅ ሀረም ጀመረ። በአባይ አሮንቃ አንድ ቦይ ከመቆፈሩ የተነሣ ሞኤሪስ ሐይቅ ተፈጠረ።
በ1850 ዓክልበ. ግድም ዋና ሚኒስትሩ ቀቲ ነበረ። «የራይንድ ስነ ቁጥር ፓፒሩስ» የተባለው ጽሑፍ በኒመዓትሬ ዘመን ነበር የተቀነባበረው።
ማኔጦን በኋላ ዘመን በግሪክኛ ሲጽፍ አመነመስ ይለዋል። በመጨረሻው ዓመት ልጁን 4 አመነምሃት የጋርዮሽ ፈርዖን አደረገው።
ቀዳሚው 3 ሰኑስረት |
የግብፅ ፈርዖን | ተከታይ 4 አመነምሃት |
-
የኒመዓትሬ ምስል
-
የኒመዓትሬ እስፊንክስ
-
የኒመዓትሬ ምስል
-
የኒመዓትሬ ምስል