ቀቲ ወይም አቅቶይ በ9ኛው ሥርወ መንግሥት (ምናልባት 2350-2331 ዓክልበ. ግድም) የገዛ የግብጽ ፈርዖን ነበረ። ዋና ከተማው በሄራክሌውፖሊስ (ግብጽኛኸነን-ነሱት) በስሜኑ ነበረ። የቀቲ (አቅቶይ) ስም በአንዳንድ ቅርስ ቢገኝም፣ ተወላጆቹ ሁሉ «ቀቲ» የሚል የቤተሠብ ስም ስለነበራቸው እነርሱን መለያየት አስቸጋሪ ነው፣ ሊቃውንትም ሁላቸው አይስማሙም።

በ3ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. የኖረው ታሪክ ጸሐፊ ማኔቶን ስለዚሁ ሥርወ መንግሥት ብዙ አይልም። ነገር ግን ስለ መጀመርያው ቀቲ እንዲህ ብሎ ይመሰክራል። «አቅቶይስ ከርሱ በፊት ከነበሩት ሁሉ ይልቅ አስፈሪ ሆነ፤ በመላ ግብጽ በተገኙት ሰዎች ላይ ክፋትን አደረገ፤ በመጨረሻም አብዶ በአዞ ተበላ።»

ይህ ቀቲ ደግሞ የመሪካሬ ትምህርት በተባለው ሰነድ ይጠቀሳል። ይኸው ሰነድ የአረመኔ ንጉሥ አገዛዝ ዘዴ የሚመክር ነው።

የአቅቶይ ምክር ከመሪካሬ ትምህርት ለማስተካከል

«ለግፈኛው ዝም ማለት መሥዋዕቱን ያፈርሳል፣
አምላክ በመቅደሱ ላይ ያመጸውን ይመታልና፣
እርሱ እንደሚያደርገው ሰዎች ይደርሱበታል፣
ለታቀደለት ወጥመድ ይጠግባል፣
በሚመጣው ዕለት ምንም ሞገስ አያገኝም።
መሥዋዕቱን ጠብቅ፣ አምላኩን አምልክ፣
ያስቸግረኛል አትበል፣ ዕጆችህ አይፈቱ።
አመጽ ያደረገብህስ፣ ይህ ሰማይን ማጥፋት ነው።
ሐውልት ለዘመናት ይጸናል፤
ጠላት አዋቂ ከሆነ አያጠፋውም፣
እርሱ ያደረገውን በሚከተሉት እንዲከብር በመመኘት።
ጠላት የሌለው የለም፣
የሁለቱ አገራት {የግብጽ} ገዢ ግን ጥበበኛ ነው
ሎሌዎችም ያሉት ንጉሥ ደደብ ሊሆን አይችልም።
ከልደቱ ጀምሮ ጠቢብ ነው፣
አምላክም ከአዕላፍ ሰዎች ይለየዋል።
ንጉሥነት በጎ ሹመት ነው፣
ሐውልቶቹን የሚያጸናለት ልጅ ወይም ወንድም የለውም፣
እራሱ ሌላውን የሚጠብቅ ነው እንጂ።
ሰው ለቀዳሚው ይሠራል፤
እርሱ ያደረገውን በሚከተሉት እንዲከብር በመመኘት።
በኔ ዘመን ግፈኛ አድራጎት ተሠራ፤
ጢኒስ አቅራቢያ ተፈረሰ።
በውነት ሆነ፤ በኔ በኩል ግን አልሆነም፣
ከተደረገ በኋላ ብቻ አወቅኩት።
እነሆ፣ ውጤቱ እኔ ካደረግኩ በላይ በለጠ፤
የተጎዳው ፍርስራሽ ሆኛልና፣
ያፈረሰውንም ለሚያሳድሰው ምንም ጥቅም የለም፣
ወይም ያሠራውን ለሚያፍርስ፣ ያጠፋውንም ለሚያክብር፤ ከዚሁ እራቅ።
መምታት በተመሳሳዩ ይከፈላል፤
ለሥራዎችም ሁሉ መልስ አለ።
አንዱ ትውልድ ለሌላው ያልፋል፤
ባሕርይንም የሚያውቅ አምላክ ተደብቋል።
ባለ እጅን የሚቃውም የለም፣
አይኖቹ ያዩትን ሁሉ ይመታል፤
ስለዚህ በመንገዱ ላይ አምላኩን አምልክ።
ዕቃዎች ከዕንቁና ከመዳብ ይሠራሉ፣
ማዕበል በማዕበል ይተካል፤
እንዲሠወር የተፈጠረ ፈሳሽ የለም፣
የተሠወረበት ግድብ ይጠፋ ነበርና።
ነፍስ ወደሚያውቀው ቦታ ይሔዳል፣
በትናንትናም መንገድ ላይ አይዘግይም።
በምዕራብ {በሢኦል} ያለህን አዳራሽህን አሳምር፣
በመቃብር ያለህን ሥፍራ በቅንነትና በትክክል አጌጥ፤
ልቦቻቸው በዚያው ይደገፋሉና፤
የቅን ሰው ባሕርይ ከበደለኛው በሬ በላይ ይቀበላልና።
አምላኩን {የጸሐይ ጣኦት } አገልግል፣ እርሱም ተመሳሳዩን ያደርግልሃል፣
በመሥዋዕትና በተቀረጸው ምስል አገልግለው፣
ያው ስምህን የሚያሳይ ነው፤
አምላኩም ያገለገለውን ሁሉ ያውቃል።
ለሰዎች፣ ለአምላኩ ከብት፣ አቅርብላቸው፣
እርሱ ሰማይንና ምድርን ለነርሱ ፈጠረና።
እርሱ የውኃዎቹን ሥሥት አቀነሰ፣
ለአፍንጮቻቸው የሕይወት እስትንፋስ ሰጠ፣
ከሥጋው የወጡ የርሱ አራያዎች ናቸውና።
ለልቡናቸው ጥቅም በሰማይ ያብራል፤
ሊመግባቸው ዕጽ፣ ከብት፣ አዕዋፍና ዓሳ ሠርቷል።
ጠላቶቹን ገድሏል፤ የራሱንም ልጆች አጥፍቷል
አመጽ ለማድረግ ስላቀዱ።
ለልቡናቸው ጥቅም መዓልትን ይሠራል፤
ያያቸውም ዘንድ በምኋሩ ይዞራል።
በስተኋላቸው መቅደስ ሠርቷል፤
ሲያልቅሱም ይሰማል።
ከዕንቁላል ጀምሮ ገዢዎች አደረገላችው፤
ከድካሙ ጀርባ ሸክሙን የሚያንሣ።
የሚሆነውን ለመከልከል ጥንቆላን እንደ መሣርያ ሠራላቸው፤
በሌሊትም በቀንም ጠብቀው።
የማይወዱትን እንዴት ገድሏል፣
አባባሌን ቸል አትበል፣
ስለንጉሡ ሕግጋት ቢሰጥም።
እንደ ሰው ልጅ እንድትነሣ ያስተምራል፣
የዛኔ ከሳሽ ሳይኖርብህ ትደርሰኝ ዘንድ።
የሚቅርብህን አትገድል፣ ሞገስን ስጠው፣
አማላክቱ ያውቁታልና።
በምድር የሚከናውን ከነርሱ አንድ ነው፣
ንጉሱንም የሚያገልግሉ ሰዎች አማልክት ናቸው።
ፍቅርህን በመላ ዓለም አሳድር፣
መልካም ባህርይ የሚስታወስ ነውና።
{አንድ መስመር ጠፍቶ ሊነብ አይችልም}
በአቅቶይም ቤት በሚከተሉት አፍ
'የችግሮች ዘመንን የጨረሰ' እንዲነገርልህ
ስለ ዛሬውኑ ዘመን ሲያስቡ።
እነሆ፣ ከሃሳቦቼ የተሻሉትን ነግሬሃለሁ፣
በፊትህ አኑራቸው።»
ቀዳሚው
ዋህካሬ ቀቲ
ግብፅ ፈርዖን
2350-2331 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
መሪብታዊ ቀቲ