የቻይና ነገሥታት ዝርዝር
ማስታወሻ፦ በቻይና ታሪክ ከ849 ዓመት ከክርስቶስ ልደት በፊት አስቀድሞ የሆኑት አመት ቁጥሮች ሁሉ አጠያያቂ ናቸው። ከ849 ዓክልበ. በኋላ ግን አመቶቹ በብዛት ሊወሰኑ ይቻላል። ከሥነ ቅርስ መጀመርያው የተረጋገጠው ንጉሥ ዉ ዲንግ ነው። ከ1200 ዓክልበ. የሆኑት ንግርተኛ አጥንቶች ጽሑፎች በኤሊ ቅርፊት ወይም በበሬ ትከሻ ላይ የጨረቃ ግርዶሽ ጊዜዎች ስለ ዘገቡ፣ የቻይና አጥኒዎች የዉ ዲንግን ዘመን ልክ ከ1258-1199 ዓክልበ. ወስነውታል።
አፈ ታሪካዊ ዘመን
ለማስተካከል- ኒዋ - የፉሢ ሚስት፣ ከማየ አይኅ አመለጠች
- ዮውቻው - ቤትን ማገንባት ያገኘ
- ስዊረን - የእሳት ጥቅም ያገኘ
- ፉሢ - ከሚስቱ ከኒዋ ጋራ ከማየ አይኅ አመለጠ። ከዚያ 115 ወይም 116 ዓመት እንደ ነገሠ ይባላል።
- «የነበልባል ነገሥታት» ፦ ሸንኖንግ (38 አመት)፣ ሊንኲ፣ ቸንግ፣ ሚንግ፣ ዥዕ፣ ከ፣ አይ፣ ዩዋንግ - 500 ዓመታት ያህል በጠቅላላ ይባላል
የኋሥያ ነገሥታት (አፈታሪካዊ፣ 2389-2010 ዓክልበ. ግድም)
ለማስተካከል- ኋንግ ዲ (ጎንግሱን ሽወንዩወን) - የዮሾንግ መሪ፣ ያንዲ ዩዋንግን በባንጯን ውግያ አሸንፎ ዮሾንግንና ሸንኖንግን በኋሥያ አዋሀደ። 99 ዓመት ነግሠ።
- ሻውሃው - 84 አመት ነገሠ? (በቀርከሃ ዜና መዋዕል ዘንድ ምናልባት 7 ዓመት ብቻ ነገሠ)
- ዧንሡ - 78 አመት ነገሠ። የኅብረተሠብ ማሻሻሎች ሠራ
- ዲ ኩ - 60 ወይም 70 አመት ነገሠ (63 በቀርከሃ ዜና መዋዕል)፤ ትምህርት ቤቶች ሠራ
- ዲ ዥዕ - 9 ዓመት
- ያው - 99 አመት ነገሠ (በ73ኛው አመት ዙፋኑን ለተከታዩ ሹን መልቀቁን በቀርከሃ ዜና መዋዕል ይዘገባል)
- ሹን - 50 ዓመት፤ ሕግ አወጣ
የሥያ ሥርወ መንግሥት (2010-1611 ዓክልበ. ግድም)
ለማስተካከልየሥያ ሥርወ መንግሥት | ||
የንጉሥ ስም | የአመታት ቁጥር | ነጥቦች |
---|---|---|
ዳ ዩ | 45 | አገሩን በ9 ጠቅላይ ግዛቶች ከፋፈለ። |
ጪ | 10 ወይም 16 | የዳ ዩ ልጅ |
ታይ ካንግ | 19 ወይም 29 | የጪ ልጅ |
ዦንግ ካንግ | 13 | የታይ ካንግ ወንድም፤ የፀሃይ ግርዶሽ በ5ኛው አመት |
ሥያንግ | 28 | የዦንግ ካንግ ልጅ። ከርሱ በኋላ ቻይና 40 ዓመት ያለ ንጉሥ ነበር። |
ሻውካንግ | 21 | የሥያንግ ልጅ |
ዡ | 17 | |
ኋይ | 26 ወይም 44 | |
ማንግ | 18 ወይም 58 | |
ሤ | 25 | |
ቡ ጅያንግ | 59 | የሤ ልጅ |
ጅዮንግ | 18 ወይም 21 | የቡ ጅያንግ ወንድም |
ጂን | 21 | የጅዮንግ ልጅ |
ኮንግ ጅያ | 31 | |
ጋው | 11 | |
ፋ | 11 ወይም 19 | የምድር መንቀጥቀጥ |
ጄ | 31 ወይም 52 | ዝሙትና ጨካኝ ንጉሥ |
የሻንግ ሥርወ መንግሥት (1611-1054 ዓክልበ ግድም)
ለማስተካከልየሥያ ሥርወ መንግሥት | ||
የንጉሥ ስም | የአመታት ቁጥር | ነጥቦች |
---|---|---|
ታንግ | 11 | መንግሥቱን ከጄ ያዘ |
ዋይ ቢንግ | 2 ወይም 3 | የታንግ ልጅ |
ዦንግ ረን | 4 | የዋይ ቢንግ ወንድም |
ታይ ጅያ | 12 ወይም 33 | የዦንግ ረን ወንድም ልጅ |
ዎ ዲንግ | 19 ወይም 29 | የታይ ጅያ ልጅ |
ታይ ገንግ | 5 ወይም 25 | የዎ ዲንግ ወንድም |
ሥያው ጅያ | 17 | የታይ ገንግ ወንድም |
ዮንግ ጂ | 12 | የታይ ገንግ ልጅ |
ታይ ዉ | 75 | የዮንግ ጂ ወንድም |
ዦንግ ዲንግ | 9 ወይም 11 | የታይ ዉ ልጅ |
ዋይ ረን | 10 ወይም 15 | የዦንግ ዲንግ ወንድም |
ሄ ዳን ጅያ | 9 | የዋይ ረን ልጅ |
ዙ ዪ | 19 | የሄ ዳን ጅያ ወንድም |
ዙ ሢን | 14 ወይም 16 | የዙ ዪ ልጅ |
ዎ ጅያ | 5 ወይም 20 | የዙ ሢን ወንድም |
ዙ ዲንግ | 9 ወይም 32 | የዙ ሢን ልጅ |
ናን ገንግ | 6 ወይም 29 | የዎ ጅያ ልጅ |
ያንግ ጅያ | 4 ወይም 17 | የዙ ዲንግ ልጅ |
ፓን ገንግ | 28 | ምናልባት 1298-1271 ዓክልብ. ነገሠ። |
ሥያው ሢን | 3 | |
ሥያው ዪ | 11 | |
ዉ ዲንግ | 59 | ሕጉን አሻሸለ። 1258-1199 ዓክልበ. አካባቢ |
ዙ ገንግ | 11 | |
ዙ ጅያ | 20 ወይም 33 | |
ሊን ሢን | 4 ወይም 6 | |
ገንግ ዲንግ | 6 ወይም 8 | |
ዉ ዪ | 35 | |
ወን ዲንግ | 11 | |
ዲ ዪ | 26 | |
ዲ ሢን | 32 ወይም 52 | ስድና ጨካኝ ንጉሥ |
የዦው ሥርወ መንግሥት (1054-229 ዓክልበ.
ለማስተካከልየዦው ሥርወ መንግሥት | ||
የንጉሥ ስም | ዘመን ዓክልበ. | ነጥቦች |
---|---|---|
ዦው ዉ | 1054-1051 ግ. | መንግሥቱን ከዲ ሢን ያዘ |
ዦው ቸንግ | 1050-1029 ግ. | |
ዦው ካንግ | 1029-1004 ግ. | |
ዦው ዣው | 1003-985 ግ. | |
ዦው ሙ | 984-930 ግ. | |
ዦው ጎንግ | 930-908 ግ. | |
ዦው ዪ (ጂ ጅየን) | 907-900 ግ. | |
ዦው ሥያው | 899-894 ግ. | |
ዦው ዪ (ጂ ሤ) | 894-886 ግ. | |
ዦው ሊ | 886-849 | ክፉና ጨካኝ ንጉሥ |
የጎንግሄ እንደራሴነት | 849-836 | |
ዦው ሡዋን | 835-790 | |
ዦው ዮው | 790-780 | |
ዦው ፒንግ | 780-728 | |
ዦው ኋን | 728-705 | |
ዦው ዧንግ | 705-690 | |
ዦው ሢ | 690-685 | |
ዦው ኊ | 685-660 | |
ዦው ሥያንግ | 659-627 | |
ዦው ጪንግ | 627-621 | |
ዦው ኳንግ | 620-615 | |
ዦው ዲንግ | 614-594 | |
ዦው ጅየን | 593-580 | |
ዦው ሊንግ | 579-553 | |
ዦው ጂንግ (ጂ ጒ) | 553-528 | |
ዦው ዳው | 528 | |
ዦው ጂንግ (ጂ ጋይ) | 527-484 | |
ዦው ዩወን | 483-477 | |
ዦው ዠንዲንግ | 476-450 | |
ዦው አይ | 449 | |
ዦው ስዕ | 449 | |
ዦው ካው | 448-434 | |
ዦው ወይሌ | 433-410 | |
ዦው አን | 409-384 | |
ዦው ሌ | 383-377 | |
ዦው ሥየን | 376-329 | |
ዦው ሸንጂንግ | 328-323 | |
ዦው ናን | 322-264 |
የጪን ሥርወ መንግሥት (229-214 ዓክልበ.)
ለማስተካከልየሃን ሥርወ መንግሥት (214 ዓክልበ. - 212 ዓ.ም.)
ለማስተካከልጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |