ታይ ካንግ
ታይ ካንግ (ቻይንኛ፦ 太康) በጥንታዊ ቻይና የሥያ ሥርወ መንግሥት ፫ኛ ንጉሥ ነበር።
የቀርከሃ ዜና መዋዕል በተባለው ጽሑፍ ዘንድ፣ አባቱ ጪ ካረፈ በኋላ (1985 ዓክልበ. ግድም) ልጁ ታይ ካንግ ተከተለው። ግቢው በዠንሡ ነበር። በዘመኑ ከልዎ ወንዝ ማዶ ለረጅም ወራት እያደነ መኮንኑ ሆውዪ መጥቶ በዠንሡ ተቀምጦ አቃወመው። «የ፭ቱ ልጆች መዝሙር» የሚባለው ግጥም ስለዚሁ ሁኔታ ነው። ታይ ካንግ አራት ዓመት ብቻ ከነገሠ በኋላ ሞተ። ወንድሙ ዦንግ ካንግ ተከተለው።
ቀዳሚው ጪ |
የሥያ (ቻይና) ንጉሥ | ተከታይ ዦንግ ካንግ |