ቡ ጅያንግ
ቡ ጅያንግ (ቻይንኛ፦ 不降) በጥንታዊ ቻይና የሥያ ሥርወ መንግሥት ዘመን ንጉሥ ነበር።
የቀርከሃ ዜና መዋዕል በተባለው ጽሑፍ ዘንድ፣ ለዘመኑ የተዘገቡት ድርጊቶች እንዲህ ናቸው፦ በ1745 ዓክልበ. ግድም አባቱ ሤ ዓርፎ ቡ ጅያንግ ተከተለው። በ፮ኛው ዓመት (1740 ዓክልበ. ግ.) በጅዩይወን አገር ላይ ዘመተ። በ፴፭ኛው ዓመት (1711 ዓክልበ.ግ.) የዪን አገረ ገዥ የጲን አገረ ገዥ አሸነፈ።
በ፶፱ኛው ዓመት (1687 ዓክልበ. ግ.) ዙፋኑን ተወና ወንድሙ ጅዮንግ ተከተለው። ንጉሥነቱን በፈቃዱ ስለ ተወ እንደ ጠቢብ ይቆጠራል። በጅዮንግ ፲ኛው ዓመት (1678 ዓክልበ. ግ.) ቡ ጅያንግ ዓረፉ። የቡ ጅያንግ ልጅ ኮንግ ጅያ በኋላ በ1661 ዓክልበ. ግ. ንጉሥ ሆነ።
ቀዳሚው ሤ |
የሥያ (ቻይና) ንጉሥ | ተከታይ ጅዮንግ |