ታይ ገንግ (ቻይንኛ፦ 太庚) በጥንታዊ ቻይና የሻንግ ሥርወ መንግሥት ንጉሥ ነበር።

ቀርቀሃ ዜና መዋዕል እና በሢማ ጭየን ታሪካዊ መዝገቦችም ዘንድ ለ5 ዓመት ከወንድሙ ዎ ዲንግ ቀጥሎ ነገሠ፤ ወንድሙም ሥያው ጅያ ተከተለው። ሆኖም እንዲያውም ዘመኑ ለ25 ዓመት እንደ ቆየ ይታሥባል።

በሥነ ቅርስ ከ1200 ዓክልበ. የተገኙት «ንግርተኛ አጥንቶች» ጽሑፎች ላለፉት ነገሥታት መሥዋዕት ሲዘረዝሩ ዎ ዲንግን አይጠቅሱትም፤ ታይ ገንግም ከቡ ቢንግ (ዋይ ቢንግ) ቀጥሎ ያደርጉታል።

ቀዳሚው
ዎ ዲንግ
የሥያ (ቻይና) ንጉሥ
1562-1537 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሥያው ጅያ