ዦንግ ካንግ (ቻይንኛ፦ 仲康) በጥንታዊ ቻይና የሥያ ሥርወ መንግሥት ፬ኛ ንጉሥ ነበር።

የቀርከሃ ዜና መዋዕል በተባለው ጽሑፍ ዘንድ፣ ወንድሙ ታይ ካንግ ካረፈ በኋላ (1981 ዓክልበ. ግድም) ዦንግ ካንግ ተከተለው። ዋና ከተማው በዠንሡ ቆየ። በዘመኑ በ፭ኛው ዓመት በ1976 ዓክልበ. ሙሉ የፀሐይ ግርዶሽ በሥያ ተከሠተ። ይህ በ5 November 1969 BC ግሪጎሪያን ካሌንደር የተከሠተው ሊታወቅ ይቻላል። የቻይና ሥነ ከዋክብት መምህሮች ግን ያንጊዜ በመረንነትና በስካር ስለ ኖሩ፣ ይህንን ግርዶሽ እንደሚደርስ በደንብ አላወቁም። ተግባራቸውን ቸል ስላደረጉ ዦንግ ካንግ የሥነ ከዋክብት ሚኒስቴር መሪዎችን እንዲቀጣቸው አለቃውን የዪን መኮንን ላከው። ይህን የሚገልጽ ሰነድ «የዪን ቅጣት ዘመቻ» ይባላል። ዦንግ ካንግ ፯ አመት ከገዛ በኋለ አረፈና ልጁ ሥያንግ ተከተለው።

ቀዳሚው
ታይ ካንግ
የሥያ (ቻይና) ንጉሥ ተከታይ
ሥያንግ