(ቻይንኛ፦ 桀) በጥንታዊ ቻይና የሥያ ሥርወ መንግሥት ዘመን መጨረሻ ንጉሥ ነበር።

ንጉሥ ጄ ጦር ይዞ በሁለት ሴቶች ላይ ሲቀመጥ፣ በ150 ዓም ግድም እንደ ተሳለ

ጄ ጭካኔና መረንነት የወደደ አምባገነን በመሆኑ ይታወሳል። በየቀኑ ብዙ ውድ ምግቦች እና አረቄ ከሩቅ አገር እንዲቀርብለት አዘዘ፣ ትክክል ካልሆነ ብዙ አገልጋዮች አስገደለ። አረቄ እየጠጣ በሰው ጀርባ እንደ ፈረስ ይሸከም ነበር። አንዲት ቁባቱ ሞ ሢ የክፋቱ አባል ሆነች። የአረቄ ሐይቅ እንዲሠራ እንዳዘዙ ይባላል፤ በጀልባ ከዞሩበት በኋላ 3000 አገልጋዮች ፈጽመው እንዲጠጡት አዘዘች፣ ሁላቸው ወድቀው ሲሰጠሙ ሳቀችባቸው። በኋላ እሷን ትቶ የሚንሻን አገረ ገዥ ሁለት ሴት ልጆች ለራሱ ቃመ።

በ10ኛው ዓመቱ 1633 ዓክልበ. የመሬት መንቀጥቀጥና የበረቅ ካፍያ ወይም ተወርዋሪ ኮከብ ተዘገቡ። በ14ኛው ዓመት 1629 ዓክልበ. ጄ ዋና ከተማውን ከዠንሡን ወደ ሆ ወንዝ ደቡብ ተዛወረ። አገልጋዮች በሚሸከሙ መቀመጫ እንደ ፈርዖኖች ይጓዝ ጀመር።

ስለ አገዛዙ በጣም ስለ ተጠላ አንዱ መኮንን የሻንግ ልዑል ሃይለኛ ሊሆን ቻለ። ብዙ ወገኖች ታማኝነት ከሥያ ንጉሥ ወደ ሻንግ ግዛት ይዛወሩ ነበር። በ15ኛው ዓመት 1627 ዓክልበ. ታንግ የሻንግ ንጉሥ ሆነ፣ በመጨረሻም በ1611 ዓክልበ. የሻንግ ሃያላት በሥያ ላይ በሚንግትያው ውግያ አሸነፉዋቸው። ታንግ ንጉስ ጄን ወደ ስደት አባረረውና ያንጊዜ የመላው ቻይና ንጉሥ ሆነ።

ቀዳሚው
የሥያ (ቻይና) ንጉሥ
1642-1611 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ታንግ