ኋንግ ዲ (ቻይንኛ፦ 黃帝 «ቢጫው ንጉሥ») በቻይና ልማዳዊ አፈ ታሪክ ዘንድ የቻይና ሕዝብ አባትና ንጉሥ ነበረ። የቤተሠቡ ስም «ጎንግሱን» የተሰጠው ስም «ሽወንዩወን» ነበር ይባላል። አባቱ ሻውድየን ተባለ።

ቢጫው ንጉሥ

የተወለደው ሾው ጪው በተባለ ሥፍራ በጩፉ ሲሆን በኋላ ነገዱን ወደ ዥዎሉ ወሰደው፤ በዚያ ገበሬ ሆኖ ድብነብርና ባለክንፍ አንበሣ የመሰለ ፍጡር አንዳስለመደ የሚል ትውፊት አለ። ያንጊዜ የኋንግ ዲ ወገን እና የያንዲ (ዩዋንግ) ወገን ለቢጫው ወንዝ ሸለቆ ተወዳዳሪዎች ነበሩ። ሦስተኛ ወገን - የ ሕዝብና ንጉሣቸው ቺ ዮው - ደግሞ ጠላቶቻቸው ሆኑ። ሦስት ውግያዎች ተከተሉ። በመጀመርያው የቺ ዮው ሥራዊት ያንዲውን አሸነፈው። ከዚያ ያንዲው ተሸንፎ ወደ ኋንግ ዲ ሸሸ። በሁለተኛው የዥዎሉ ውግያ ኋንግ ዲ እና ቺ ዮው ተጋጠሙ። በዚህ ውግያ ቺ ዮው ጉምን በጥንቆላ ፈጥሮ ኋንግ ዲ እንደገና በተነው፣ ብዙም ሌሎች ጉድ ሥራዎች እንደ ተከሠቱ የሚል ትውፊት አለ። ቺ ዮው በዚህ ውግያ ቢሸነፍም፣ የኮርያ ሕዝብና የህሞንግ ሕዝብ ዛሬውንም እንደ ቅድማያታቸው ይቆጥሩታል። በሦስተኛው የባንጯን ውግያ፣ ኋንግ ዲ በያንዲው ላይ ድል አደረገ። ከዚያ በኋላ ወገኖቻቸው ተባብረው የኋሥያ ብሔር (የቻይና ሕዝብ ቅድማያቶች) ፈጠሩ። ኋንግ ዲ በይፋ የቻይና ንጉሥነት ማዕረግ ወሰደ፤ የዘውድና ቤተ መንግሥት ሥርዓት ጀመረ።

ከዚህ በተረፈ ኋንግ ዲ ጋሪመርከብ እንደ ፈጠረ ይጻፋል። ደግሞ ምኒስትሩ ጻንግችየ መጀመርያ የቻይና ጽሕፈት ፈጠረ፤ የኋንግ ዲ ሚስት ሌዙም ልብስ ከሃር ትል እንዴት እንደሚሠራ አሳየች። የህክምና መጽሓፍ ኋንግዲ ኔጂንግ ሌሎችንም መጻሕፍት እንደ ጻፈ ይታመናል። ከዚህ በላይ የቻይና ስነ ፈለክየቻይና ዘመን አቆጣጠር ፈጠረ። ስለ ኋንግ ዲ ብዙ ሌሎች ትውፊቶች አሉ።

መጀመርያ ሚስቱ ሌዙ ተከታዩን ሻውሃውን ወለደች። 3 ሌሎች ሚስቶች እነርሱም ፋንግሌ፣ ቶንግዩ እና ሞሙ ነበሩት። በተለመደው ታሪክ ዘንድ ለ99 አመት ነገሠ። ታላቅ መቃብሩ በያንአን ከተማ ሲገኝ እስከ ዛሬ ድረስ በየአመቱ በሥነ ስርአት ይከብራል።

የኋንግ ዲ ዘመነ መንግሥት በቀርከሃ ዜና መዋዕል ዘንድ

ለማስተካከል
 
የኋሥያ ውኅደት ዘመን

የቀርከሃ ዜና መዋዕል የሚባሉት ጥንታዊ መዝገቦች በኋንግ ዲ ዘመን ይጀምራሉ።

  • በመጀመርያው አመት (2389 ዓክልበ. ግድም) ዋና ከተማው ዮሾንግ (የአሁን ሺንዠንግ) ነበረ። ንጉሣዊ ወግ ልብስ - መጎናጸፊያውና ከቆብ የተንጠለጠለ ጌጥ - መሰረተ።
  • 20ኛው አመት (2370 ዓክልበ.) - የደመቀ ደመናት ምልክት በሰማይ ታይቶ መኳንንቱን እንደ ደመናዎች ቀለሞች ሰየማቸው።
  • 59ኛው አመት (2331 ዓክልበ.) - «የተቀደዱ ደረቶች»ና «ረጅም እግሮች» የተባሉት ወገኖች ለኋንግ ዲ ተገዙ።
  • 77ኛው አመት (2313 ዓክልበ.) - የኋንግዲ ልጅ ቻንግዪ (የዧንሡ አባት) ወደ ስሜን ወደ ርዎ ሽዌ ወንዝ ወጣ።
  • 100ኛው አመት (2290 ዓክልበ) - ኋንግ ዲ ዐረፈ፤ የምድር መንቀጥቀጥ ነበረ።

ኋንግ ዲ 7 አመት ከአረፈ በኋላ፣ ሚኒስትሩ ጻንግችየ ዧንሡን ንጉሥ እንዳደረገው ይባላል።

ቀዳሚው
የለም (መሥራች)
ኋሥያ (ቻይና) ንጉሥ ተከታይ
ሻውሃው