ዦንግ ረን (ቻይንኛ፦ 仲壬) በጥንታዊ ቻይና የሻንግ ሥርወ መንግሥት ንጉሥ ነበር።

ቀርቀሃ ዜና መዋዕል እና በሢማ ጭየን ታሪካዊ መዝገቦችም ዘንድ ለ4 ዓመት ከወንድሙ ዋይ ቢንግ ቀጥሎ ነገሠ፤ የዳ ዲንግም ልጅ ታይ ጅያ ተከተለው። ዪ ዪን በዚህ ዘመን ሁሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሆን ቀረ።

ዳሩ ግን በሥነ ቅርስ ከ1200 ዓክልበ. የተገኙት «ንግርተኛ አጥንቶች» ጽሑፎች ላለፉት ነገሥታት መሥዋዕት ሲዘረዝሩ ዦንግ ረንን አይጠቁትም፤ ታይ ጅያም ከዋይ ቢንግ በፊት ያደርጉታል። ሆኖም ዳ ዲንግ ሳይነግሥ እንዳረፈ፣ ዪ ዪንም ያለመቋረጥ ከታንግ ጀምሮ እስከ ዎ ዲንግ ድረስ (1628-1581 ዓክልበ.) እንደ ሻንግ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዳገለገለ ትክክለኛ ስለሚመስል ቅደም-ተከተሉ ሢማ ጭየን እንዳለው መሆን አለበት።

ቀዳሚው
ዋይ ቢንግ
የሥያ (ቻይና) ንጉሥ
1597-1593 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ታይ ጅያ