ዲ ኩ
በሽጂ በሲማ ጭየን
ለማስተካከልበ100 ዓክልበ. ሲማ ጭየን በጻፈው የታላቁ ታሪክ ጸሐፊ መዝገቦች ወይም ሽጂ እንደሚለን፣ የጋውሢን አባት ጅያውጂ ወልደ ሻውሃው ወልደ ኋንግ ዲ ነበር። ከሕጻንነቱ ጀምሮ መናገር ይችል ነበር። ከዧንሡ በኋላ ንጉሥ («ዲ») ኩ የሚለው ስም ወሰደ። ዲ ኩ ለጋሥ፣ አስተዋይ፣ ጨዋ፣ ደግ፣ ቅን ገዢ ይባላል፣ የዘመን መቆጠሪያ ፈጠረ። ልጆቹ ያውና ዥዕ ነበሩ። በኩ መሞት ዥዕ ተከተለው፣ ነገር ግን ዥዕ መጥፎ ንጉሥ ሆኖ ወንድሙ ያው ተከተለው።
በቀርከሃ ዜና መዋዕሎች
ለማስተካከልየቀርከሃ ዜና መዋዕል በተባለው ጽሑፍ ዘንድ፣ ጋውሢን ወይም ኩ ሲወለድ ድርብ ተርታ ጥርሶች ነበሩት፣ እጅግ ጥበበኛ ነበር። በንጉሥ ዧንሡ ዘመን ጋውሢን የሲን ልዑል ሆነ። ዧንሡ ካረፈ በኋላ (2206 ዓክልበ.) የሸንኖንግ ትውልድ ሹቄ ሁከት አነሣ፣ ነገር ግን ጋውሢን አጠፋውና ንጉሥ ሆነ። ዋና ከተማው በፑ ነበር። ዕውሮች በከበሮና በደወል ሙዚቃ እንዲሠሩ ያድርግ ነበር። በ16ኛው አመት (2190 ዓክልበ.) አለቃው ቹንግ የጎረቤቱን አገር ዩኳይን አጠፋ። በ45ኛው አመት (2161 ዓክልበ.) ልጁን የታንግ ልዑል (ያው) ተከታዩ እንዲሆን አደረገው። ሆኖም በ63ኛው አመት በኩ መሞት (2143 ዓክልበ.) ሌላ ልጁ ዥዕ ተከተለው። ዥዕ ለ9 ዓመታት ነግሦ ግን ከዙፋኑ ተጣለና ወንድሙ ያው ተተካ።
ዋቢ መጽሐፍት
ለማስተካከልየታላቁ ታሪክ ጸሐፊ መዝገቦች በሲማ ጭየን (እንግሊዝኛ)
ቀዳሚው ዧንሡ |
የኋሥያ (ቻይና) ንጉሥ | ተከታይ ዲ ዥዕ |