ዲ ዥዕ (ቻይንኛ፦ 帝挚) በቻይና አፈ ታሪክ የጥንታዊ ቻይና ንጉሥ ነበር።

100 ዓክልበ. ሲማ ጭየን የጻፈው የታላቁ ታሪክ ጸሐፊ መዝገቦች (ሽጂ) እና የቀርከሃ ዜና መዋዕል ስለ ዥዕ ብዙ ባይሉንም 2ቱ መጻሕፍት ይስማማሉ። አባቱ ዲ ኩ («ንጉሥ ኩ») ካረፈ በኋላ የተመረጠው ልጁ የታንግ ልዑል (ያው) ያንጊዜ አልተከተለም፣ ነገር ግን የኩ ሌላ ልጅ የያው ወንድም ዥዕ ዙፋኑን ያዘ። («ንጉሥ») ዥዕ መጥፎ ንጉሥ ሲሆን ለ9 ዓመታት ብቻ (2142-2133 ዓክልበ. ግድም) ነግሦ ከዙፋኑ ተጣለና ወንድሙ ያው ተተካ።

ቀዳሚው
ዲ ኩ
ኋሥያ (ቻይና) ንጉሥ ተከታይ
ያው