ጂን
ጂን (ቻይንኛ፦ 廑) በጥንታዊ ቻይና የሥያ ሥርወ መንግሥት ዘመን ንጉሥ ነበር። ሌላ ስሙ ዪንጅያ ነበር።
የቀርከሃ ዜና መዋዕል በተባለው ጽሑፍ ዘንድ፣ ለዘመኑ የተዘገበው እንዲህ ነው፦ በመጀመርያው ዓመት በሆ ወንዝ ምዕራብ ኖረ። በ፬ኛው ዓመት «የምዕራብ ሙዚቃ» ቃነ፤ የኩንዉና ወይ ገዥ ጂ ታን ወደ ሹዦው ተዛወረ። በ፰ኛው ዓመት (1661 ዓክልበ.) በታምራዊ ትርዒት አሥር ፀሐዮች አብረው በሰማይ ታዩ፤ በዚያም አመት ጂን ዓረፈና የአጐቱ ቡ ጅያንግ ልጅ ኮንግ ጅያ ተከተለው።
ቀዳሚው ጅዮንግ |
የሥያ (ቻይና) ንጉሥ 1669-1661 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ ኮንግ ጅያ |