(ቻይንኛ፦ 杼) በጥንታዊ ቻይና የሥያ ሥርወ መንግሥት ዘመን ንጉሥ ነበር።

የቀርከሃ ዜና መዋዕል በተባለው ጽሑፍ ዘንድ፣ በ1885 ዓክልበ. ግድም አባቱ ሻውካንግ ዓርፎ ዡ ተከተለው፤ ዋና ከተማው በይወን (አሁን ጂይወን) ቆየ። በ፭ኛው ዓመት ዋና ከተማው ወደ ላውጪው (አሁን ካይፈንግ) አዛወረው። በ፰ኛው ዓመት ወደ ምሥራቅ ባሕር ዘመተ፤ አንድ ባለ ዘጠኝ ጅራት ቀበሮ እንዳዳነ ይባላል። በ፲፫ኛው ዓመት የወንዝ ሥራዎች ሚኒስትሩ፣ የሻንግ መስፍን ሚንግ ዓረፈ። በ፲፯ኛው ዓመት ዡ ዓረፈና ልጁ ኋይ ተከተለው።

ቀዳሚው
ሻውካንግ
የሥያ (ቻይና) ንጉሥ
1885-1869 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ኋይ