ኅዳር ፲፮
ኅዳር ፲፮ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፸፮ኛ ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፺ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፹፱ ቀናት ይቀራሉ።
ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች
ለማስተካከልበዚህ ዕለት በዓለም ዙሪያ ብዙ ተፈጥሮአዊ ሁከቶች የብዙ ሕዝቦችን ሕይወት ማጥፋታቸው በታሪክ ተመዝግቧል። ለምሣሌ፦
- በ፲፫፻፴፮ ዓ.ም. በሰሜናዊ የሜዲተራንያን ባሕር በተለይም ከኢጣልያ በስተምዕራብ በሚገነው የቲሬኖ ባሕር ሥር የተነሳ የመሬት እንቅጥቅጥ ያስከተለው የባሕር መናወጥ (tsunami)፣ አካባቢውን አጥፍቷል።
- በ፲፯፻፶፪ ዓ.ም. በሜዲተራንያን ባሕር አካባቢ የተነሳ የመሬት እንቅጥቅጥ ቤይሩትንና ደማስቆን ሲያወድም ከሠላሣ እስከ አርባ ሺህ ሰዎች ፖተዋል።
- በ፲፰፻፴፪ ዓ.ም. በሕንድ አገር ላይ የተነሳው ጥቅል አውሎንፋስ የኮሪንጋን ከተማ ሲያወድም፣ የተከተለው የውቅያኖስ ሞገድ ደግሞ ወደሃያ ሺህ የሚጠጉ መርከቦችን ጠራርጓል። ወደ ሦሥት ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ሞተዋል።
- በ፲፱፻፲፱ ዓ.ም. በአሜሪካ ታሪክ ሃይለኛው የኅዳር ጥቅል አውሎንፋስ ተነስቶ በመካከለኛ - ምዕራባዊ ግዛቶች በጠቅላላው ሰባ ስድስት ሰዎች ሲሞቱ ከአራት መቶ በላይ ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል። የጉዳቱ ብሶት በአርካንሳስ ግዛት ውስጥ በምትገኘው ‘ሀርብ ስፕሪንግስ’ ላይ ሲሆን አምሣ አንዱ ሟቾች ከዚያው ግዛት ነበሩ።
- በ፲፱፻፵፫ ዓ.ም. በሰሜናዊ ምሥራቅ አሜሪካ በሰዐት መቶ ስድሳ ኪሎሜትር ፍጥነት ያለው ንፋስ ያስከተለው የበረዶ ነበልባል የሦስት መቶ ሃያ ሦስት ሰዎች የሞት ምክንያት ሆኗል።
- በ፲፱፻፹ ዓ.ም. በሰዐት ሁለት መቶ ስድሳ አምስት ኪሎሜትር ፍጥነት ባለው ነፋስ የተነዳችው “ኒና”፣ (Super Typhoon Nina) የተባለችው አውሎንፋስ የፊሊፒን ደሴቶች ላይ የከሰተችው ቁጣ ወደ አንድ ሺህ ሠላሣ ሰዎችን ገድሏል።
ሌላ ታሪካዊ ማስታወሻዎች
ለማስተካከል- ፲፱፻፶፮ ዓ.ም. - በዳላስ፣ ቴክሳስ ላይ በሰው እጅ የተገደሉት ሠላሣ አምሥተኛው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ በአርሊንግተን ብሔራዊ መቃብር በታላቅ ሥነ ስርዐት ተቀበሩ። በዚሁም የቀብር ስርዐት ለመሳተፍ ከዓለም ዙሪያ ብዙ መሪዎች መጥተው ነበር። ከነዚህም መሃል የፈረንሳይ ፕሬዚደንት ሻርል ደ ጎል፤ የአየርላንድ ፕሬዚደንት ደ ቫሌራ፤ የምዕራብ ጀርመን ቻንስለር ኤርሃርድና የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ይገኙበት ነበር።
- ፲፱፻፶፰ ዓ/ም - በእስራኤል፤ ፈረንሳይ፤ ብሪታኒያ፤ ምዕራብ ጀርመን፤ ስዊድን እና ጃፓን መንግሥታት ዕርዳታ የተገነባው የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ሕንፃ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተመርቆ ተከፈተ። [1]
- ፲፱፻፸፯ ዓ.ም. - በኢትዮጵያ ውስጥ ለተከሰተው ታላቁ ድርቅና ረሐብ እርዳታ እንዲሆን በብሪታንያ ሠላሣ ስድስት የሙዚቃ ባለሙያዎች “ባንድ ኤይድ” በሚል ስም ተሰባስበው፤ “የክርስቶስ ልደት መሆኑን ያውቁታል ወይ?” (Do They Know It's Christmas) የተባለውን ዘፈን ቀረጹ።
ልደት
ለማስተካከል- ፲፱፻፵፬ ዓ.ም. - ደራሲው አጥናፍሰገድ ኪዳኔ አዲስ አበባ ተወለደ።
ዕለተ ሞት
ለማስተካከል- ፲፱፻፷፯ ዓ.ም. - የበርማ ተወላጅ የነበሩት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ዩ ታንት በስድሳ አምሥት ዓመታቸው አረፉ።
- ፲፱፻፺ ዓ.ም. - የማላዊ የዕድሜ ልክ ፕሬዚደንት የነበሩት ሄስቲንግስ ካሙዙ ባንዳ በዚህ ዕለት አረፉ።
ዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል- ^ Selected Speeches of His Imperial Majesty Haile Selassie I, 1918-1967 - page 522 –
- (እንግሊዝኛ) http://news.bbc.co.uk/onthisday/hi/dates/stories/november/25/newsid_3211000/3211440.stm
- (እንግሊዝኛ) http://www.nytimes.com/learning/general/onthisday/big/1125.html#article
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |