ቭላዲሚር ሌኒን
(ከሌኒን የተዛወረ)
ቭላድሚር ኢሊች ኡሊኖቭ በቀላሉ ሌኒን (1862 - 1916) ሩሲያዊ ጠበቃ፣ አብዮተኛ እና የቦልሼቪክ ፓርቲ መሪ የነበር ሰው ነው። የሶቪየት ህብረት እና ሩሲያን በ1909 የተቆጣጠረው የኮሚዩኒስት ሥርዓት የመጀመሪያ መሪ ነበር። የሌኒን አስተሳሰቦች አሁን ሌኒኒዝም በመባል ይታዎቃሉ።
የሕይዎት ታሪክ
ለማስተካከልቀደምት ሕይዎቱ
ለማስተካከልሌኒን በ፲፰፻፷፪ ዓም ከአስተማሪ እናቱ እና የትምህርት ባለስልጣን ከነበሩት አባቱ ተወለደ። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በሚከታተልበት ወቅት ስለፓለቲካ አብሮ ማጥናት ጀመረ። በዚህ ዎቅት ሌኒን በትምህርቱ ጎበዝ የነበር ሲሆን የላቲን እና ግሪክ ቋንቋዎችን ያጠና ነበር። በ፲፰፻፸፱ ዓ.ም የሩሲያን ገዢ ወይንም ዛር ስለተቃዎመ ከትምህርት ቤት ተባረረ። እርሱ ግን በግሉ መጻሕፍትን ማንበቡንና አዳዲስ አሳቦችን ለራሱ ማስተማሩን አላቋረጠም ነበር። ስለሆነም በ፲፰፻፹፪ ዓም የሕግ ጠበቃ ለመሆን የሚያስችል ፈቃድ (ላይሰንስ) አገኘ።
ሌኒን ከዩኒቨርሲቲ በተባረረበት በዚያው ዓመት፣ የርሱ ወንድም የነበረው አሌክሳንደር እንዲሁ ዛር አሌክሳንደር ሳልሳዊን በቦምብ ለመግደል ሲያሴር ተይዞ ተሰቀለ። እህቱም በግዞት ወደ ታታርስታን ተላከች። ሌኒን በዚህ በጣም ከመበሳጨቱ የተነሳ ፣ የወንድሙን ሞት ለመበቀል ቃል ገብቶ ነበር።