ሚያዝያ ፴
(ከሚያዝያ 30 የተዛወረ)
ሚያዝያ ፴ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፵ ኛው ዕለትና የወርኅ ፀደይ (በልግ) ፴፭ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ሉቃስ ፻፳፮ ቀናት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመን ማርቆስ ደግሞ ፻፳፭ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፰፻፸፬ ዓ/ም - እምባቦ በሚባል ሥፍራ የሸዋው ንጉሥ ምኒልክ ሠራዊት እና የጎጃም ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ሠራዊት ውጊያ ገጥሞ ድሉ የንጉሥ ምኒልክ ሲሆን፣ ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ተማረኩ። [1]
- ፲፱፻፳፭ ዓ/ም - የሕንድ አባት በሚል ቅጽል ስም የሚታወቀው ሞሃንድራስ ካራምቻንድ ጋንዲበአገሩ የእንግሊዝን አስተዳደር በመቃወም የሃያ አንድ ቀን የ'ረሀብ አድማ' ጀመረ።
- ፲፱፻፴፯ ዓ/ም - በአውሮፓ የሁለተኛው የዓለም ጦርነትን ማክተም ምክንያት በማድረግ 'ሴቲፍ' በተባለች የአልጄሪያ ከተማ በተካሄደ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ፻፫ አውሮፓውያን በመሞታቸው፣ የገዢው የፈረንሳይ መንግሥት ፖሊሶች እና ወታደሮች ባካሄዱት ጨካኝ በቀላ እስከ ስድስት ሺ አልጄሪያውያን ተጨፍጭፈዋል። የዚህ አረመኔያዊ ድርጊት ሳቢያ በመላው የሰሜን አፍሪቃ የፈረንሳይን ቅኝ ገዢነት ማክተሚያ አብሳሪ እንደሆነ ታሪካውያን ይዘግባሉ።
ልደቶች
ለማስተካከልማጣቀሻዎች
ለማስተካከል- ^ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፣ ዕለታዊ የታሪክ ድርጊት - የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ፓትረያርክ (፲፱፻፶፩ ዓ/ም)፣ገጽ ፻፵፰
- ^ (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/190144 Ethiopia: Annual Review for 1965
- ^ (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1829 Ethiopia: Annual Review for 1974
ዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል- (እንግሊዝኛ) http://en.wikipedia.org/wiki/May_8
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |