ጥቅምት ፪
(ከጥቅምት 2 የተዛወረ)
ጥቅምት ፪ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፴፪ኛው ዕለት እና የመፀው ፯ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ሉቃስ ፫፻፴፬ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ዮሐንስ ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፴፫ ዕለታት ይቀራሉ።
- ፲፯፻፸፫ዓ/ም - በካሬቢያን ባሕር ላይ የተነሳው የአውሎ ንፋስ ማዕበል በማርቲኒክ እና በባርቤዶስ ደሴቶች ላይ ሲጎርፍ እስከ ፳፪ ሺ ሰዎች ጠፍተዋል።
- ፲፰፻፶፪ ዓ/ም - ዓፄ ቴዎድሮስ በሸዋ ላይ በአቶ ሰይፉ (ሰይፈ ሥላሴ) ሣህለ ሥላሴ መሪነት በኃይል ሥልጣን የያዘውን ሠራዊት ለመውጋት ገብተው አንኮበር ሙቅ ምድር ከሚባለው ሥፍራ ጦርነት ገጥመው የሸዋው ወገን ድል ሲሆን፣ ንጉሠ ነገሥቱ ከተማውን አስዘርፈው ከዳተኛ የተባሉትን የምርኮኞችን ቀኝ እጅ እና ግራ እግራቸውን አስቆረጡ። ስለዚህ ድርጊት አንዲት አልቃሽ፦ «ዓፄ ቴዎድሮስ እጅግ ተዋረዱ፤ የሸዋን ሰው ኹሉ እጅ ነስተወት ሄዱ» ብላ ገጠመች።
ልደት
ለማስተካከልዕለተ ሞት
ለማስተካከል- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና ፓትሪያርክ፣ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ በዚህ ዕለት አረፉ።
ዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል- ተክለጻድቅ መኩሪያ፣ ዓፄ ቴዎድሮስ እና የኢትዮጵያ አንድነት (፲፱፻፹፩ ዓ/ም)፣ ገጽ ፻፺፮-፯
- {{en]] P.R.O., FCO 371/1829 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1974
- {{en]] P.R.O., FCO 371/784 Annual Review of 1970
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |