ብሔራዊ መዝሙር
ብሔራዊ መዝሙር ማለት የአንዱ ሀገር ሕዝብ አገራቸውን ይሚያከብሩበት ይፋዊ ዘፈን ነው።
አሁን ከሚገኙት ብሔራዊ መዝሙሮች መካከል፣ የጃፓን ብሔራዊ መዝሙር ወይም «ኪሚጋዋ» ከሁሉ ጥንታዊ የሆነው ግጥም አለው፤ ቃሎቹም በ912 ዓም ታተሙ። ዜማው ግን በ1872 ዓም ተቀነባበረ፤ በ1880 ዓም ደግሞ ይፋዊ የጃፓን መዝሙር መጀመርያ ተደረገ።
በፖላንድ መዝሙሩ «ቦጉሮድዚጻ» በ970 ዓም እንደ ተቀነባበረ ይታመናል። ከሁሉ ጥንታዊው ጽሑፍ ቅጂ ከ1400 ዓም ያህል እንደ ሆነ ይታመናል። ይህ እስከ 1787 ዓም እስከ ፖላንድ መጀመርያ ውድቀት ድረስ ይቀጠል ነበር።
የኔዘርላንድ መዝሙር «ውልሄመስ» በ1560 ግድም ተጽፎ ቢሆንም እስከ 1924 ዓም ድረስ ይፋዊ አልተደረገም፤ እስካሁንም ድረስ ይፋዊ ነው።
በ1581 ዓም የ«ማርሽ ፬ኛው አንሪ» ዜማ ተጻፈ፤ እስከ 1784 ዓም ድረስ እንደ ፈረንሳይ ብሐራዊ መዝሙር አገለገለ።
እስካሁን ድረስ የብሪታንያ መዝሙር የሆነው «ጎድ ሰይቭ ዘ ኲን» የተጻፈው በ1611 ዓም ያህል እንደ ነበር ይታመናል፤ ከ1737 ዓም ጀምሮ እንደ ብሔራዊ መዝሙር አገልግሏል።
ከነዚህም በኋላ ከ1700ዎችና 1800ዎች ጀምሮ ብሐራዊ መዝሙሮች በአውሮፓና በመላው ዓለም ዘመናዊ ሆኑ።