ንግድ
የእቃወች ግዢ እና ሽያጭ
ንግድ በመሰረቱ እጅግ በጣም ጥንታዊ የሰው ልጆች እንቅስቃሴ ነው። ሰው ማንኛውንም የፈለገውን ቁሳቁስ ማሙዋላት የማይችል ስለሆነ የግድ በተሰማራበት ሙያ የሚያገኘውን የስራ ውጤት ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ነገር ግን እሱ ራሱ ማምረት የማይችላቸውን ነገሮች ለማግኘት ሲል የሚያካሄደው የምርቶች ልውውጥ ሂደት ነው።
- ደግሞ ይዩ፦ ምጣኔ ሀብት
ታሪክ
ለማስተካከል- 3000 ዓክልበ. ግድም - በጥንታዊ ግብጽ ሠራተኞች ከፈርዖን መንግሥት የነጭ ሽንኩርት፣ ሽንኩርት ወዘተ. መቁነን በየቀኑ ይቀበላሉ። ይህም ለምግብ፣ እንዲሁም አንድላይ ለገንዘብና ለዘር (ለማትረፍ) ያገልግላል። ለመንግሥት የተመለሰውም ግብር (በሽንኩርት ወዘተ. ተከፍሎ) ለደህንነት በፒራሚድ መዝገቦች ውስጥ ይከማች ነበር።
- 2460 ዓክልበ. ? - ኦሬክ ገብስን ወደ አራታ አገር ይልካል፤ በምላሽም እንቁን ይጠይቃል። ስላልተላከ ግን ጦርነት ተከተለ (ኤንመርካርና የአራታ ንጉሥ - አፈ ታሪክ)
- 2375 ዓክልበ. ግድም - ሱመር እህልን ለኤላም ከብት በመለዋወጥ የዓለም መደበኛ ገበያ ተመሠረተ። በቅርብ ጊዜ ሱፍ፣ ብረታብረት (በተለይ ብር፣ ወርቅ፣ ቆርቆሮ፣ መዳብ)፣ እና ባርያዎች ይጨመራሉ።
- 2300 ዓክልበ. ግ. - የድልሙን መርከቦች እንጨት ከማዶ ባህር ወደ ላጋሽ ያስገቡ ጀመር።
- 2100 ዓክልበ. ግ. - አንድ ካሩም (የንግድ ጣቢያ ሠፈር) በኤብላ ግዛት ይመሠረታል።
- 2075 ዓክልበ. ግ. - የአካድ ነጋዴዎች ወገን በቡሩሻንዳ (በሐቲ) ይጠቀሳሉ።
- 2003 ዓክልበ. ግ. - የ3 መንቱሆተፕ ተጓዦች ዕጣን፣ ሙጫና ሽቶ ከፑንት ወደ ምስር ማምጣት ጀመሩ።
- 1985 ዓክልበ. ግድም - ከእሳት በኋላ ብዙ ብር በፒሬኔ ተራሮች ተገኝቶ ለፊንቄ ሰዎች በርካሽ ተነገደ። (ዲዮዶሮስ ሲኩሉስ - አፈ ታሪክ)
- 1983 ዓክልበ. - የኡር-ናሙ ሕግጋት መደበኛ ምና = ስልሳ ሰቀል (የክብደት ልክ) ደነገገ።
- 1900-1740 ዓክልበ. ግ. - የአሦር ንጉሥ ኢሉሹማ በርካታ ብረታብረት ወደ መስጴጦምያ አስገባ፤ ከዚያ ጀምሮ አሦራውያን ካሩም በካነሽና ሐቲ አስተዳደሩ።
- 1900-1740 ዓክልበ. - ሴማውያን ነጋዴዎች የንግድ ጣቢያ ሠፈር በጌሤም በስሜን ግብጽ መሠረቱ። እስከ ኩሽ መንግሥት ድረስ ንግድ አካሄዱ።
- 1900 ዓክልበ. ግ. ? - የፈተና ደንጊያ ዕውቀት በሃራፓ ሥልጣኔ (ፓኪስታን) ተገኘ።
- 1775 ዓክልበ. ግ. - የኤሽኑና ሕግጋት መደበኛ የልውውጥ ዋጋዎች ደነገገ።
- 1704 ዓክልበ. - የባቢሎን ንጉሥ ሐሙራቢ ሕግጋት ሰው ሁሉ ለገዛው ዕቃ ሁሉ ደረሰኝ በሸክላ ጽላት እንዲጠበቅ በሞት ቅጣት ለማስገድ ሞከረ። (§7)
- 1200 ዓክልበ. ግ. - የፈተና ድንጊያ በግብጽ ታወቀ።
- 700 ዓክልበ. ግ. - የፈተና ድንግያ በኬልቲካ (ፈረንሳይ)ና በተለይ በልድያ ይታወቃል።
- 630 ዓክልበ. ግ. - የልድያ መንግሥት መጀመርያ የወርቅና የብር መሐለቅ ፈጠረ።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |