ዓረብኛ
(ከአረብኛ የተዛወረ)
ይህ መጣጥፍ ምንም ዓይነት የዋቢ ምንጮች አያካትትም። እባክዎን ተገቢ ምንጮን በመጥቀስ ያሻሽሉት። (፬ ነሐሴ ፳ ፻ ፮) |
ዓረብኛ (العربية) ፡ የሴማዊ ፡ ቋንቋዎች ፡ ቤተሠብ ፡ አባል ፡ ሆኖ ፡ የዕብራይስጥ ፡ የአረማያ ፡ እንዲሁም ፡ የአማርኛ ፡ ቅርብ ፡ ዘመድ ፡ ነው። ፪ ፻ ፶ (250) ፡ ሚሊዮን ፡ የሚያሕሉ ፡ ሰዎች ፡ እንደ ፡ እናት ፡ ቋንቋ ፡ ይናገሩታል። ከዚህም ፡ በላይ ፡ በጣም ፡ ብዙ ፡ ሰዎች ፡ እንደ ፡ ፪ኛ ፡ ቋንቋ ፡ ተምረውታል። የሚጻፈው ፡ በዓረብኛ ፡ ፊደል ፡ ነው። በዓረብ ፡ አለም ፡ ውስጥ ፡ አያሌ ፡ ቀበሌኞች ፡ ይገኛሉ።
ቋንቋው ፡ በእስልምና ፡ ታላቅ ፡ ሚና ፡ አጫውቷል። እስላሞች ፡ አላህ ፡ ለሙሐማድ ፡ ቁርዓንን ፡ ሲገልጽ ፡ በዓረብኛ ፡ እንደ ፡ ሆነ ፡ ስለሚያምኑ ፡ እንደ ፡ ቅዱስ ፡ ቋንቋ ፡ ይቆጥሩታል። አብዛኛው ፡ ዓረብኛ ፡ ተናጋሪዎች ፡ ሙስሊሞች ፡ ናቸው።
ዛሬ ፡ በምዕራብ ፡ ዓለም ፡ ደግሞ ፡ ብዙ ፡ ሰዎች ፡ አረብኛ ፡ እያጠኑ ፡ ነው። በታሪክ ፡ ከፍተኛ ፡ ሚና ፡ በማጫወቱ ፡ መጠን ፤ ብዙ ፡ የዓረብኛ ፡ ቃላት ፡ ወደ ፡ ሌሎች ፡ ቋንቋዎች ፡ ገብተዋል።