1907
(ከ፲፱፻፯ የተዛወረ)
1907 አመተ ምኅረት
- መስከረም 3 - በ1ኛ አለማዊ ጦርነት የደቡብ አፍሪካ ጭፍሮች ጀርመን ደቡብ-ምዕራባዊ አፍሪካ (ናሚቢያ) ወረሩ።
- መስከረም 3-18 - በፈረንሣይ ታላቅ የኤይን ወንዝ መጀመርያ ውግያ
- መስከረም 28 - ጀርመኖች የበልጅክ ከተማ አንትወርፐን ማረኩ
- ጥቅምት 17 - ቱርኮች የሩሲያ ጥቁር ባሕር ወደቦች ደብደቡዋቸው
- ጥቅምት 23 - በአንደኛው የዓለም ጦርነት ሩሲያ በቱርክ ላይ ጦርነት አወጀ
- ጥቅምት 22 - በአንደኛው የዓለም ጦርነት የብሪታንያ መርከቦች ኮሮኔል በሚባለው ውጊያ በቺሌ አጠገብ በጀርመን መርከቦች ተሸነፉ
- ጥቅምት 25 - እንግሊዝና ፈረንሳይ በቱርክ ላይ ጦርነት አዋጁና እንግሊዝ ቆጵሮስን ያዘች
- ጥቅምት 26 - ጃፓናውያን የጀርመኖች ቦታ በቻይና ጅያውጆውን ወሰዱባቸው
- ኅዳር 12 - የአሜሪካ ሠራዊት ከቬራክሩዝ ሜክሲኮ ወጡ
- ጥር 5 - በአቨዛኖ ጣልያ ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ 32,610 ሰዎች አጠፋ
- ጥር 11 - የጀርመን ጸፐሊን የእንግሊዝ አገር ከተሞች በቦምብ ደበደበ
- ጥር 23 - ጀርመኖች በሩሲያ ላይ የመርዝ ጋዝ ፈሰሰች
- መጋቢት 5 - የብሪታንያ መርከቦች በቺሌ አጠገብ የጀርመን መርከብ ድሬስዴንን አሰመጡት
- መጋቢት 5 - ብሪታንያ ፈረንሳይና ሩሲያ በስምምነት ቁስጥንጥንያ ከጦርነቱ በኋላ ለሩሲያ መንግሥት እንዲሆን ተስማሙ
- መጋቢት 9 - እንግሊዞች በዳርዳኔል ቱርክ ላይ ሲወረሩ አልተከናወንም
- ሚያዝያ 5 - በሜክሲኮ አብዮት - በሠላያ ውግያ የፓንቾ ቪላ ሠራዊት ድል ሆኑ
- ሚያዝያ 14 - ጀርመኖች በኢፕር በልጅክ ውግያ የመርዝ ጋዝ ጣሉ
- ሚያዝያ 16 - የአርሜኖች እልቂት በቱርክ ጀመረ
- ሚያዝያ 17 - የአውስትራልያና የኒው ዚላንድ ሠራዊት በጋሊፖሊ ቱርክ ወረሩ
- ሚያዝያ 22 - የአውስትራልያ ንኡስ-መርከብ በቱርክ አጠገብ ተሰጠመ
- ሚያዝያ 29 - የእንግሊዝ መርከብ ሉሲታኒያ በአይርላንድ አጠገብ ተሰጥማ 1,198 ሞቱ
- ግንቦት 1 - ጀርመንና ፈረንሳይ ሃያላት በአርቷ ውጊያ ተጣሉ
- ግንቦት 15 - ጣልያ በአውስትሪያ-ሃንጋሪ ላይ ጦርነት በማዋጁ የጓደኞች ቡድን አባል ሆነ
- ግንቦት 26 - በሜክሲኮ አብዮት - በሌዮን ውግያ የፓንቾ ቪላ ሠራዊት ድል ሆኑ
- ሐምሌ 21 - የአሜሪካ ሠራዊት የካሪቢያን አገር ሃይቲ ወረሩ
- ሐምሌ 29 - በታላቅ አውሎ ንፋስ 275 ሰዎች በኒው ኦርሊንስና ጋልቬስቶን ቴክሳስ አሜሪካ አገር ጠፉ
- ነሐሴ 10 - የጓደኞች ቡድን በስምምነት ቦስኒያ እና ክሮዋሽያ ከጦርነቱ በኋላ ለሰርቢያ እንዲሆኑ ተስማሙ
- ጳጉሜ 1 - ታንክ የሚባል የጦርነት መሳርያ ለመጀመርያ ጊዜ በእንግሊዞች ተፈተነ።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |