ሚያዝያ ፭
(ከሚያዝያ 5 የተዛወረ)
ሚያዝያ ፭፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፲፭ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፲ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፶፩ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፶ ቀናት ይቀራሉ።
በዚህ ዕለት ኢትዮጵያዊው ማኅሌታይ ቅዱስ ያሬድ ስለተወለደ ከድጓው ድርሰቱ የተወሰደ ቅንጣቢ፦
መፀው/መከር
"በጊዜሁ ኀለፈ ክረምት ቆመ በረከት ናሁ ጸገዩ ጽጌያት" (ሲተረጐም) ክረምቱ በጊዜው አለፈ አሁን የበረከት ጊዜ ይሆናል አበባዎችም ያብባሉ፡፡
- ፲፱፻፵፫ ዓ.ም. ፦ ፪ ሺህ ፻፷፰ ወታደር የያዘው የኢትዮጵያ የክቡር ዘበኛ ሠራዊት የሻለቃ ጦር ወደ ኮርያ ዘመተ፡፡ ከዘማቾቹ ማህል አንዱ የነበረው ‘የክራሩ ጌታ’ የ፶ ዐለቃ ካሣ ተሰማ "እልም አለ ባቡሩ" በሚለው ዘፈኑ ይሄንን ዕለት አወድሶታል።
- ፲፱፻፶፮ ዓ/ም - አንጋፋው የፊልም ተዋናይ ሲድኒ ፗቲዬር ‘ሊሊስ ኦፍ ዘ ፊልድ’ (Lilies of the Field) በተባለው ፊልሙ የ’ኦስካር’ ሽልማት ሲቀበል የመጀመሪያው ጥቁር አሜሪካዊ ነው።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት (አ. አ.ድ) ((እንግሊዝኛ)፡ Organisation of African Unity (OAU)) የአፍሪቃ የሠራተኞች ማኅበራት የአንድነት ውል አዲስ አበባ ላይ ተፈረመ።
- ፳፻፬ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታዮች በዛሬው ዕለት የኢየሱስ ክርስቶስን ስቅለት በጾም፤ ስግደት እና ጸሎት ይዘክራሉ።
ልደት
ለማስተካከልዕለተ ሞት
ለማስተካከልዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል- መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፣ ዕለታዊ የታሪክ ድርጊት - የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ፓትረያርክ (፲፱፻፶፩ ዓ/ም)
- (እንግሊዝኛ) http://www.thepeoplehistory.com/april12th.html Archived ኦገስት 13, 2011 at the Wayback Machine
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1660 ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1973
- http://www.ethiopianreporter.com Archived ጃንዩዌሪ 24, 2005 at the Wayback Machine ኪንና ባህል፡ ሳምንቱ በታሪክ
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |