አየርላንድ
(ከአይርላንድ የተዛወረ)
አየርላንድ አትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ የሚገኝ ደሴት ነው። ከታላቋ ብሪታንያ በቀኝ በኩል በሰሜን ቻናል፣ በአይሪሽ ባህር እና በየቅዱስ ግዮርጊስ ቻናል ይለያል። ከብሪታኒያ ደሴቶች አየርላንድ በስፋት ሁለተኛ ሲሆን ከአውሮፓ ሶስተኛ እንዲሁም ከዓለም ሃያኛ ነው።
የአየርላንድ ደሴት ለሁለት ይከፈላል፦ የአየርላንድ ሪፐብሊክ (አየርላንድ) እና ሰሜን አየርላንድ። የአየርላንድ ሪፐብሊክ የደሴቱን አምስት ስድስተኛ ያካትታል፡፡ ሰሜን አየርላንድ የዩናይትድ ኪንግደም አካል ነው። በ2022 የደሴቱ የህዝብ ብዛት ከሰባት ሚሊዮን በለጥ ያለ ነበር። ከነዚህም ውስጥ 5.1 ሚሊዮን ሰዎች የአየርላንድ ሪፐብሊክ የሚኖሩ ሲሆን 1.9 ሚሊዮኑ በሰሜን አየርላንድ ይኖራሉ። ይሄም በህዝብ ብዛት በአውሮፓ ከታላቋ ብሪታኒያ ቀጥሎ ሁለተኛ ያደርገዋል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |