ጥቅምት ፳፪
(ከጥቅምት 22 የተዛወረ)
ጥቅምት ፳፪ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፶፪ኛው እና የመፀው ፳፯ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፫፻፲፬ ቀናት ሲቀሩ፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፲፫ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፭፻፭ ዓ.ም. - በቫቲካን ውስጥ የሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ ካቴድራል፣ በልዩ ሲስቲን ጸሎት ቤት ጣሪያ ላይ በሚካኤል አንጀሎ የተሳለው ታሪካዊ ስዕል ለመጀመሪያ ጊዜ ለሕዝብ ታየ።
- ፲፱፻፳፫ ዓ/ም - በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የንግሥ በዓል ዋዜማ፤ የታላቁ ንጉሠ ነገሥት የዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ሐውልት በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አጠገብ፤ ለበዓል የመጡት እንግዶች በተገኙበት ሥርዐት፣ የሐውልቱን መጋረጃ የመግለጥ ክብር ለብሪታንያ ንጉሥ ወኪል ለ(ዱክ ኦፍ ግሎስተር) ተሰጥቶ ሐውልቱ ተመረቀ።
- ፲፱፻፵፭ ዓ.ም. - አሜሪካ በዓለም የመጀመሪያውን የሃይድሮጅን ቦምብ በማፈንዳት ማርሻል ደሴቶች (Marshall Islands) ላይ ፈተነች።
- ፲፱፻፶፫ ዓ.ም. - በአሜሪካ የፕሬዚደንትነት ምርጫ ዘመቻቸው ላይ ለዕጩነት የቀረቡት ጆን ኤፍ ኬኔዲ፣ የሰላማዊ ተልእኮ ወይም (Peace Corps) በሚል ያቀዱትን ኃሣብ ይፋ አደረጉ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም
- - የጀርመን ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ (ምሥራቅ ጀርመን) አዲስ አበባ ላይ ቤተ-ልዑካን (ኤምባሲ) ከፈተ።
- - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ቤጂንግ የበረራ መሥመር ጀመረ።
- - የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በጎ አድራጎት ድርጅት የዓመቱ ሽሽልማት ተቀባይ፣ የሴኔጋል ፕሬዚደንት ሊዮፖልድ ሴዳር ሴንግሆር አዲስ አበባ ገቡ።
- - የቆጵሮስ ደሴት ፕሬዚደንት አቡነ መቃሪዮስ የንጉሠ ነገሥቱን ፵፫ኛ የዘውድ በዐል ያካተተ የአምስት ቀን ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ ገቡ።
- ፲፱፻፸፬ ዓ.ም. - በካሪቢያ ባሕር ላይ የሚገኙት የአንቲጋ እና ባርቡዳ ደሴቶች ነጻነታቸውን ከብሪታንያ ተቀዳጁ።
ልደት
ለማስተካከልዕለተ ሞት
ለማስተካከል- ፲፱፻፸፪ ዓ.ም. - የሠላሳ አራተኛው የአሜሪካ ፕሬዚደንት የድዋይት ዴቪድ አይዘንሃወር ባለቤት ሜሚ አይዘንሃወር በተወለዱ በ ሰማንያ ሁለት ዓመታቸው አረፉ።
- ፳፻ ዓ.ም - በሁለተኛው የዓለም ጦርነት መደምደሚያ ላይ ሂሮሺማ ላይ የአቶም ቦምብ የጣለውን የአሜሪካ አየር ኃይል ዠበብ ያበረሩት ብርጋዴር ጄኔራል ፖል ቲቤትስ (Brigadier Gen. Paul Tibbets) በተወለዱ በዘጠና ሁለት ዓመታቸው አረፉ።
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |
ዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1660 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1973