ሰኔ ፴ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻ ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፷፮ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፷፭ ቀናት ይቀራሉ።

አቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች

ለማስተካከል

፲፰፻፴፰ ዓ/ም አንድ የሜክሲኮ ሠራዊት ምሽግ ከተማረከ በኋላ የአሜሪካ ሕብረት መንግሥት የካሊፎርኒያን ግዛት አጠቃሎ መያዙን አወጀ።

፲፰፻፶፯ ዓ/ም ፕሬዚደንት አብራሃም ሊንከንን ከገደላቸው ጆን ዊልክስ ቡዝ ጋር በግድያው ለመተባበራቸው በሕግ የተፈረደባቸው አራት ሰዎች ዋሺንግተን ዲ.ሲ ላይ በስቅላት ተቀጡ።

፲፰፻፺ ዓ/ም የአሜሪካ ሕብረት መንግሥት የሃዋይን ደሴቶች ከግዛቱ ጋር ደረበ።

፲፱፻፺፯ ዓ/ም በለንደን የሕዝብ መጓጓዣ ድር ላይ በተፈጸመው የሽብርተኞች ፍንዳታ በሦስት ውስጠ-ምድር ባቡር ጣቢያዎችና በአንድ ወጥቶ-እብስ ላይ አምሳ ስድስት ሰዎች ሲሞቱ፣ ከሰባት መቶ በላይ ሌሎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ዕለተ ሞት

ለማስተካከል

ዋቢ ምንጮች

ለማስተካከል


የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ