ዛሬውን በሰፊ ጥቅም ላይ ያሉት የዓለም ጽሕፈቶች በ5 ዋና መደቦች ሊካፈሉ ይችላሉ። እነዚህም፦

በሰፊው ለመመልከት ስዕሉን ይጫኑ
  ሃንጉል (የኮርያ ጽሕፈት)
  ሌሎች አልፋቤቶች
  የዐረብ ጽሕፈት (አብጃድ)
  ሌሎች አብጃዶች
  ደቫናጋሪ ጽሕፈት ('አቡጊዳ' የተባለ)
  ሌሎች 'አቡጊዳዎች'
  የቻይና ጽሕፈት (ሎጎግራፊክ)

ሎጎግራፊክ ጽሕፈቶች ለማስተካከል

ሎጎግራፊክ ጽሕፈቶች እያንዳንዱ ምልክት ወይም ሎጎግራም ለአንድ ቃል ይቆማል። የግብጽ ሃይሮግሊፎች መጀመርያ ከሎጎግራም (ስዕሎች) ብቻ ተሠራ። ዕጅግ በጥንት ቅድመ-ታሪክ ዘመን ግን የተናባቢ ምልክቶች እና የክፍለ-ቃል ምልክቶች ተጨመሩለት።

በሌሎቹ ጥንታዊ ሎጎግራም ጽሕፈቶች ደግሞ እያንዳንዱ ምልክት ለቃል ወይም ለክፍለ-ቃል ሆኖ ይጻፍ ነበር። ከነዚህም የትንሹ እስያ ሃይሮግሊፍኩነይፎርም ጽሕፈትየማያ ሃይሮግሊፍ አሉ።

ኣሁን የቻይና ጽሕፈት እንዲሁም ከሎጎግራም ይሠራል። የቻይና ጽሕፈት ከቻይንኛ ጭምር ለሌሎች ልሳናት እንደ ቬትናምንኛኮሪይኛ ቀድሞ ይጠቀም ነበር። ዛሬም የቻይና ምልክቶች በጃፓንኛ ጽሕፈት ደግሞ ይገኛሉ። በቻይና ዙሪያ ሌሎች ተመሳሳይ ጽሕፈቶች ዪ ጽሕፈትታንጉት ጽሕፈት፤ የናቂ ጽሕፈት ይገኛሉ።

ሲላቢክ ጽሕፈቶች ለማስተካከል

በሲላቢክ ጽሕፈቶች እያንዳንዱ ምልክት ለአንድ ክፍለ-ቃል ይጠቅማል።

በ'ጥሬ ሲላቢክ' ጽሕፈቶች፣ እነኚህ ምልክቶች ለአንድ ድምጽ አይመሳሰሉም። ስለዚህ «ቴ... ታ... ቶ...» የሚሉ ፊደላት ከቶ አይመሳሰሉም፣ ለምሳሌ በጃፓንኛ በሚጠቅመው «ካታካና» በሚባል ጽሕፈት፤ እነዚህ ድምጾች テ , タ, ト ይጻፋሉ። ጃፓንኛ ደግሞ ሌላ «ሂራጋና» በተባለ ሲላቢክ ጽሕፈት ሊጻፍ ይችላል።

ሌሎች ጥሬ ሲላቢክ ጽሕፈቶች በጥንት የቆጵሮስ ጽሕፈት (Mycaenaean Greek Linear B) እና ኩነይፎርም፤ ዛሬም፦

አቡጊዳዎች ለማስተካከል

በቋንቋ ጥናት በቅርቡ አቡጊዳ የሚለው ቃል ከኢትዮጵያ ልሳናት ተወስዶ ሌላ ትርጉም ተሰጥቶታል። በዚህ መደብ እያንዳንዱ ክፍለ-ቃል ለተመሳሳይ ድምጽ ተመሳሳይ ቅርጽ ኖሮት ይመሳሰላሉ። እያንዳንዱ ፊደል ከአንድ መሠረት ቅርጽ ጀምሮ በየአናባቢው ይለወጣል ማለት ነው። ስለዚህ ቴ... ቱ... ታ... (እንደ ግዕዝ ጽሕፈት) ሲመሳሰሉ ይታያሉ።

በዚህም መደብ ውስጥ ከኢትዮጵያ ፊደሎች ጭምር በሕንድ ዙሪያ የተገኙት ብራህሚክ ጽሕፈቶች (ዴቫናጋሪ ወዘተ.) እና የካናዳ ኗሪዎች ጽሕፈት ይከተታሉ።

አልፋቤቶች ለማስተካከል

አብጃዶች ለማስተካከል

በአብጃዶች እያንዳንዱ ምልክት ለአንድ ተናባቢ ይጠቅማል። አብጃዶች ከሁሉ አስቀድሞ የተለመደው የአልፋቤት አይነት ነበር። በመጀመርያ አብጃዶች አናባቢዎቹ አልተጻፉም ነበር። በዛሬው አብጃዶች ግን (የዕብራይስጥ አልፋቤትየአረብኛ አልፋቤት ወዘተ...) አናባቢዎቹ በልዩ ልዩ ተጨማሪ ምልክታት ሊታዩ ይቻላል።

አብጃዶች ለሴማዊ ቋንቋዎች የተፈጠሩ ናቸው። ከሌሎች አብጃዶች መካከል፦

በቀድሞውም፦

ሙሉ ፊደላት ለማስተካከል

በሙሉ ፊደላት (ባለ-አናባቢ አልፋቤቶች) እያንዳንዱ ምልክት ለተናባቢ ወይም ለአናባቢ ይጠቅማል። ስሙ ከግሪክ አልፋቤት መጀመርያ 2 ፊደላት አልፋ እና ቤታ መጣ። የላቲን አልፋቤት ደግሞ ሙሉ ፊደል ነው። ከሌሎቹም ዛሬ፦


በጥንትም፦

ቦፖሞፎ አልፋቤት በታይዋን ለቻይንኛ ሲጠቀም በከፊል ሲላቢክ ነው። በድሮ በእስፓንያ የነበሩ ጽሕፈቶች (የተርቴሶስ አልፋቤት ወዘተ.) ሙሉ ፊደሎች ሳይሆኑ በከፊል ሲላቢክ ነበሩ።

ደግሞ ይዩ ለማስተካከል