የቻይና ጽሕፈት
የቻይና ጽሕፈት በተለይ ቻይንኛን ለመጻፍ የተደረጀው ጽህፈት ዘዴ ነው። ዛሬም የቻይና ምልክቶች በጃፓንኛ ጽሕፈት ደግሞ ይገኛሉ። የቻይና ጽሕፈት ቀድሞ ለሌሎች ልሳናት እንደ ቬትናምንኛ፣ ኮሪይኛ ይጠቀም ነበር።
የቻይና ጽሕፈት ሎጎግራም ከተባሉት ምልክቶች ይሠራል። በጥንታዊ ቻይንኛ፣ እያንዳንዱ ምልክት ለአንድ ቃል ቆመ፣ የእያንዳንዱም ቃል እርዝማኔ አንድ ቀለም ብቻ ነበር እንጂ ለአንድ ቃል ሁለት ክፍለ ቃላት አልነበሩትም። አሁን በዘመናዊ ቻይንኛ፣ እያንዳንዱ ምልክት አንድ ቀለም ወይም ክፍለ-ቃል ሲሆን ብዙዎች ቃላት ግን ከአንድ ምልክት ወይም ቀለም በላይ ይኖራቸዋል። በጃፓንኛ የአንዱ ቻይናዊ ምልክት ድምጽ እራሱ በርካታ ቀለሞች ሊኖሩት ሲችሉ፣ ሲላቢክ ከሆኑት ከሌሎች ጽሕፈቶች ጋር ይቀላቀላል።
በአጠቃላይ ምናልባት 50 ሺህ ምልክቶች ቢኖሩም፣ አብዛኛው ጊዜ ከቀን ቀን የሚጠቀሙ 3-4,000 ብቻ ስለሆኑ እነዚህን ማወቅ ለማንበብ ችሎታ ይበቃል።
እያንዳንዱ ምልክት በቻይንኛ ልዩ ልዩ ንዑስ ቋንቋዎች ሌላ ድምጽ አጠራር ሊኖረው ይችላል፤ እንዲሁም ያው ምልክት በጃፓንኛና በሌሎቹ ልሳናት በፍጹም ሌላ ድምጽ ይኖረዋል።
በቻይንኛ መምህራን ዘንድ፣ ለምልክቶቹ ስድስት መደቦች አሉ፤ እነርሱም፡
የስዕል ምልክት
ለማስተካከልእነዚህ በቀላሉ ከነገሩ ስዕል የተደረጁ ምልክቶች ናቸው።
ቻይናዊ
ምልክት (ልማዳዊ/ የቀለለ) |
ፑቶንግኋ
ቻይንኛ አጠራር |
ትርጉም |
---|---|---|
山 | /ሻን/ | ተራራ |
人 | /ሬን/ | ሰው ልጅ |
口 | /ኮው/ | አፍ |
刀 | /ዳው/ | ቢላዎ / ሠይፍ |
木 | /ሙ/ | እንጨት |
日 | /ሪ/ | ፀሐይ / ቀን |
月 | /ይዌ/ | ጨረቃ / ወር |
女 | /ኒው/ | ሴት |
子 | /ዝር/ | ልጅ |
馬 / 马 | /ማ/ | ፈረስ |
鳥 / 鸟 | /ኛው/ | ወፍ |
目 | /ሙ/ | ዓይን |
水 | /ሽዌ/ | ውሃ |
የሀሣብ ምልክቶች
ለማስተካከልእነዚህ ሀሣቡን ከሚያሳይ ስዕል ተደረጁ
ቻይናዊ
ምልክት (ልማዳዊ/ የቀለለ) |
ፑቶንግኋ
ቻይንኛ አጠራር |
ትርጉም |
---|---|---|
一 | /ዪ/ | አንድ |
二 | /እር/ | ሁለት |
三 | /ሳን/ | ሦስት |
大 | /ዳ/ | ትልቅ |
天 | /ትየን/ | ሰማይ |
小 | /ሽያው/ | ትንሽ |
上 | /ሻንግ/ | ላይ |
下 | /ሥያ/ | ታች |
本 | /በን/ | ሥር |
末 | /ሞ/ | ጫፍ |
ውስብስብ ሀሣብ ምልክቶች
ለማስተካከልእነዚህ ከአንድ ሀሣብ ምልክት በላይ ይሠራሉ።
ቻይናዊ
ምልክት (ልማዳዊ/ የቀለለ) |
ፑቶንግኋ
ቻይንኛ አጠራር |
ትርጉም |
---|---|---|
明 | /ሚንግ/ | ብሩህ / ብርሃን / ነገ |
好 | /ሃው/ | ጥሩ |
休 | /ሥዩ/ | እረፍት |
林 | /ሊን/ | ደን |
የድምጽ ምልክቶች
ለማስተካከልእነዚህ ምልክቶች ከሌሎች ነገሮች ስዕሎች ተወሰዱ፣ በቻይንኛ የለላው ነገር ድምጽና የሀሣቡ ድምጽ ተመሳሳይ በሆኑበት አጋጣሚ ስዕሉ ተበደረ ማለት ነው። ለምሳሌ፣ ቃሉ /ሥር/ «አራት» ደግሞ እንዳጋጣሚ «ሰርን» ለማለት ይጠቅማል፣ ስለዚህ የ«ሰርን» ስዕል 四 ደግሞ ለ«አራት» ይቆማል።
ቻይናዊ
ምልክት (ልማዳዊ/ የቀለለ) |
የፑቶንግኋ
ቻይንኛ አጠራር |
ትርጉም |
---|---|---|
來/来 | /ላይ/ | መምጣት |
四 | /ሥር/ | አራት |
北 | /በይ/ | ስሜን |
要 | /ያው/ | መፈልግ |
少 | ሻው | ጥቂት |
永 | /ዮንግ/ | ዘላለም |
የስዕልና የድምጽ ምልክት ውሁድ
ለማስተካከልእነዚህ ምልክቶች ቢያንስ ከአንድ ስዕል ምልክት እናም ከአንድ የድምጽ ምልክት አንድላይ ይሰራሉ።
ቻይናዊ
ምልክት (ልማዳዊ/ የቀለለ) |
የፑቶንግኋ
ቻይንኛ አጠራር |
ትርጉም |
---|---|---|
清 | /ጪንግ/ | ግልጽ |
睛 | /ጂንግ/ | ዓይን |
菜 | /ጻይ/ | ጎመን |
沐 | /ሙ/ | መታጠብ |
淋 | /ሊን/ | ማፍሰስ |
嗎 / 吗 | /ማ/ | ወይ? (የጥያቄ ቃል) |
የተቀየረ ዘመድ ምልክት
ለማስተካከልይህ መደብ የነባር ቃል ተቀይሮ በሌላ ትርጉም ያገኙት ምልክቶች ናቸው።
ለምሳሌ፦ 考 /ካው/ «ፈተና»፣ የተቀየረው ከ 老 /ላው/ «ጥንታዊ» ነው።