ጥቅምት ፱
(ከጥቅምት 9 የተዛወረ)
ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፴፱ኛው እና የመፀው ፲፬ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ሉቃስ ፫፻፳፯ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ዮሐንስ ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፳፮ ዕለታት ይቀራሉ።
- ፲፱፻፳፰ ዓ/ም የዓለም መንግሥታት ማኅበር በግፍ ኢትዮጵያን በወረረችው ፋሺስት ኢጣልያ ላይ የዱኛ ማዕቀብ ውሳኔ አስተላለፈ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የኅብረተ-ሰብአዊት ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት፣ የቀድሞ የንጉሠ ነገሥቱን መንግሥት ባለሥልጣናት የሚዳኝ ወታደራዊ የፍትሕ ሸንጎ መሠረተ።
- ፲፱፻፸፱ ዓ/ም የሞዛምቢክን ፕሬዚደንት ሳሞራ ማሼልን እና አብረዋቸው የሚጓዙ ፴፫ ሰዎችን የጫነው አየር ዠበብ በአገሪቱ ውስጥ ሌቦምቦ ተራራ ጋር ሲጋጭ ተሳፋሪዎቹ ሕይወታቸው አልፏል።
- ፲፱፻፺፰ ዓ/ም የቀድሞው የኢራቅ ፕሬዚደንት ሳዳም ሁሴን በነፍሰ ገዳይነት እና በሰፊው በሰው ልጅ ላይ ወንጀል ሠርተዋል በመባል ፍርድ ቤት ሲቀርቡ፣ ከተከሰሱባቸው ወንጀሎች ሁሉ ነፃ መሆናቸውን መሰከሩ።
- ፲፱፻፺፱ ዓ/ም በከፍተኛ ወንጀል ተጠርጥረው በፖሊስ የሚፈለጉ ኢትዮጵያውያንን በሞያሌ በኩል ሸኝተው ለማስኮብለል የሞከሩ የውጭ ዜጋ የሆኑ ሁለት የአውሮፓ ኮሚሽን ሠራተኞች በወንጀል ከተጠረጠሩት ኢትዮጵያውያን ጋር በዛሬው እለት እጅ ከፍንጅ ተያዙ ከተባለ በኋላ የኢሚግሬሽንና ዜግነት ዋና መምሪያ ይህን ህገ ወጥ ተግባር የፈፀሙት ሁለቱ የውጪ ዜጎችም ከአገር እንዲወጡ መወሰኑን ገለፀ፡፡
ልደት
ለማስተካከልዕለተ ሞት
ለማስተካከል- ፲፱፻፸፪ ዓ.ም.ስመ ጥሩው የቡልጋ ተወላጅ አርበኛና የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ሊቀ መንበር፣ ደጃዝማች ኪዳኔ ወልደመድኅን በ ፷፬ ዓመታቸው መስኮብ ላይ አረፉ።
ዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FO 371/190144 Annual Review of 1965
- {{en]] P.R.O., FCO 371/1829 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1974
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |