መጋቢት ፳፪
መጋቢት ፳፪ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፪ ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ቀን በኋላ እስከ ዓመቱ መፈጸሚያ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፻፷፬ ቀናት ሲቀሩ፣ በ ዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፷፫ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፱፻፳፪ ዓ/ም - በዋድላ አውራጃ «አንቺም» በሚባለው ሜዳ ላይ፣ የራስ ጉግሣ ወሌ አሥር ሺ ጦር በንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት የጦር ሚኒስትር በራስ ሙሉጌታ ከሚመራው ሠላሳ ሺ ሠራዊት ጋር ገጥሞ ራስ ጉግሣ በጥይት ተመተው ሲወድቁ ሠራዊታቸው ድል ሆነ።[1]
- ፲፱፻፳፰ ዓ.ም.፣ ኢትዮጵያ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አዝማችነት ከኢጣሊያን ሠራዊት ጋር በማይጨው ጦርነት ገጠመች
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም የዓፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት፣ የታኅሣሥ ግርግር መሪ የነበሩት ሜጀር ጄኔራል መንግሥቱ ንዋይ በተሰቀሉ ማግሥት በተደረገው ሹም ሽር ጸሐፌ ትእዛዝ አክሊሉ ሀብተ ወልድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ሲሾሙ፣ በጊዜው በሎንዶን አምባሳዶር የነበሩት ልጅ እንዳልካቸው መኮንን ደግሞ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስትር ሆነው ተሾሙ። ልጅ እንዳልካቸው የ ስድሳ ስድስቱ አብዮት ሲፈነዳ ጸሐፌ ትእዛዝ አክሊሉን በመተካት ከ ሠላሳ ሦስቱ ድል በኋላ የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ሦስተኛው ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል።
- ፲፱፻፷፩ ዓ/ም - የታላቋ ብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሃሮልድ ዊልሰን፤ በናይጄሪያ ስለተቀሰቀሰው የእርስ በእርስ ጦርነት ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እና ከአፍሪቃ አንድነት ድርጅትጋር የሁለት ቀን ውይይት ለማድረግ አዲስ አበባ ገቡ። በታሪክ ኢትዮጵያን ከጎበኙት ሁለት የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትሮች፣ ዊልሰን የመጀመሪያው ናቸው።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ፓሪስ የመንገደኛ መሥመር፣ የመጀመሪያውን በረራ አከናወነ።
ልደት
ለማስተካከልዕለተ ሞት
ለማስተካከል- ፲፱፻፳፪ ዓ/ም - ራስ ጉግሣ ወሌ «አንቺም» ሜዳ ላይ በጦርነት በጥይት ተመትተው ወደቁ። ራስ ጉግሣ እስከ መስከረም ፲፯ ቀን ፲፱፻፱ ዓ/ም ድረስ የወይዘሮ ዘውዲቱ ምኒልክ ባል ነበሩ።
ዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል- ^ ዘውዴ ረታ፣ «ተፈሪ መኮንን ፦ ረዥሙ የሥልጣን ጉዞ»፣ ሦስተኛ እትም (፲፱፻፺፱ ዓ/ም)፣ ገጽ ፭፻፴፩
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/536 Annual Review of 1969
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |