ግንቦት ፲፫
ግንቦት ፲፫ ቀን፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፶፫ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፵፰ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፲፫ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፲፪ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - የየካቲት ፲፪ ቀን አዲስ አበባ ላይ ግራዚያኒ ላይ የተወረወረውን ቦምብ ምክንያት በማድረግ ፋሺስቶች ደብረ ሊባኖስ ገዳም ገብተው ፫፻፳ መነኮሳትን በግፍ ጨፈጨፉ፤ ገዳሙንም አቃጠሉ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የአሩሲ ጠቅላይ ግዛት (አሁን አርሲ) እንደራሴ ሆነው የተሾሙትን አቶ ተስፋ ቡሸን የጠቅላይ ግዛቱ ሕዝብ አባሮ አስወጣቸው።
- ፲፱፻፹፫ ዓ/ም - የኢሕዲሪ (የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ) ፕሬዚዳንትና የኢሠፓ (የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ) ዋና ጸሐፊ የነበሩት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም አገር ጥለው በመኮብለል ዚምባብዌ ገቡ።
- ፲፱፻፺፭ ዓ/ም በሰሜናዊ አልጄሪያ የተከሰተው የመሬት እንቅጥቅጥ ከሁለት ሺ በላይ ሰዎችን አጥፍቷል።
ልደት
ለማስተካከል- ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም በዚህ ዕለት አዲስ አበባ ተወለዱ።
ዕለተ ሞት
ለማስተካከልዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1829 ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1974
- http://www.ethiopianreporter.com Archived ጃንዩዌሪ 24, 2005 at the Wayback Machine ኪንና ባህል፡ ሳምንቱ በታሪክ
- መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፣ ዕለታዊ የታሪክ ድርጊት - የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ፓትረያርክ (፲፱፻፶፩ ዓ/ም)
- (እንግሊዝኛ) http://en.wikipedia.org/wiki/May_21
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |