የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ
የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ፳ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ሲሆን ከሰኔ ፭ እስከ ሐምሌ ፮ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. በብራዚል ይካሄዳል።[1] ብራዚል ይህን ውድድር ስታዘጋጅ ይሄ ሁለተኛ ጊዜዋ ነው። ፊፋ የ2014 እ.ኤ.አ. ውድድር በደቡብ አሜሪካ እንደሚካሄድ በ2007 እ.ኤ.አ. ካወጀ በኋላ ብራዚል ያለማንም ተቀናቃኝ አዘጋጅ አገር ሆና ተመርጣለች።
የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ |
|
---|---|
ይፋዊ ምልክት
|
|
የውድድሩ ዝርዝር | |
አስተናጋጅ | ብራዚል |
ቀናት | ከሰኔ ፭ እስከ ሐምሌ ፮ ቀን |
ቡድኖች | ፴፪ (ከ፭ ኮንፌዴሬሽኖች) |
ቦታ(ዎች) | ፲፪ ስታዲየሞች (በ፲፪ ከተማዎች) |
← 2010 እ.ኤ.አ. 2018 እ.ኤ.አ. → |
የ፴፩ አገራት ብሔራዊ ቡድኖች ከጁን 2011 እ.ኤ.አ. ጀምሮ የተካሄዱ የማጣሪያ ውድድሮችን በማለፍ ከብራዚል ጋር በመጨረሻው ውድድር ላይ ለመሳተፍ በቅተዋል። በጠቅላላው ፷፬ ጨዋታዎች በ፲፪ ከተማዎች ውስጥ በሚገኙ አዲስ የተገነቡ ወይም የተሻሻሉ ስታዲየሞች ይከናወናሉ። በዓለም ዋንጫ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የጎል ላይን ቴክኖሎጂ በጥቅም ላይ ውሏል።[2]
በ1930 እ.ኤ.አ. ከተካሄደው የመጀመሪያው የዓለም ዋንጫ ጀምሮ ሁሉም የዓለም ዋንጫ ሻምፕዮን አገራት (ብራዚል፣ አርጀንቲና፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሣይ፣ ጀርመን[ማስታወሻ 1]፣ ኢጣልያ፣ እስፓንያ እና ኡራጓይ) በዚህ ውድድር ውስጥ ተሳታፊ ናቸው። ከዚህ በፊት በደቡብ አሜሪካ የተዘጋጁትን ዋንጫዎች እንዳለ የወሰዱት የደቡብ አሜሪካ ቡድኖች ናቸው።[3]
ተሳታፊ አገራት እና ዳኛዎች
ለማስተካከልማጣሪያ
ለማስተካከልከጁን 2011 እስከ ኖቬምበር 2013 እ.ኤ.አ. የተካሄዱትን የማጣሪያ ጨዋታዎች ያለፉት አገራት ከውድድሩ በፊት ከያዙት ደረጃ ጋር ተዘርዝረዋል። ከነዚህ ውስጥ ቦስኒያና ሄርጸጎቪና ብቻ ከዚህ በፊት በዓለም ዋንጫ አልተሳተፈችም።[4][ማስታወሻ 2]
ኤ.ኤፍ.ሲ. ካፍ ኦ.ኤፍ.ሲ.
|
ኮንካካፍ ኮንሜቦል |
ዩኤፋ |
የምድብ ድልድል ዕጣ አወጣጥ
ለማስተካከል፴፪ቱ ተሳታፊ አገራት በአራት በ፬ ቋቶች ተደራጅተዋል። በፊፋ የብቃት ደረጃ ላይ የሚገኙት ምርጥ ፯ ቡድኖች ብራዚል ጨምረው በዘር ቋት (seeded pot) ውስጥ ተመድበዋል።[5] ቀሪዎቹ ቡድኖች በተቻለ መጠን ከተለያዩ ኮንፌዴሬሽኖች እንዲወጣጡ (ማለትም በአንድ ምድብ ውስጥ የሚገኙ አገራት በመልከዓምድር የተራራቁ እንዲሆን) በማድረግ በሌሎቹ ፫ ቋቶች ተመድበዋል።[6][7] የመደብ ድልድል ሥነ ስርዓቱ ኅዳር ፳፯ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ብራዚል በሚገኘው ኮስታ ዶ ሳዊፒ ሪዞርት ተካሄዷል።[8]
ቡድኖች
ለማስተካከልዋና መጣጥፍ፦ የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ቡድኖች
እንድ 2010 እ.ኤ.አ. ውድድር እያንዳንዱ ቡድን ፳፫ ተጫዋቾች ሲኖሩት ከነዚህም ውስጥ ፫ቱ ግብ ጠባቂ መሆን አለባቸው። እያንዳንዱ ብሔራዊ የእግር ኳስ ማህበር የሚያሰልፋቸውን ፳፫ ተጫዋቾች ውድድሩ ከመጀመሩ ፲ ቀናት በፊት ማሳወቅ ነበረበት።[9]
ቡድኖቹ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ተጫዋች ካጋጠማቸው ከመጀመሪያ ግጥሚያቸው 24 ሰዓት በፊት ድረስ መለወጥ ይችላሉ።[9]
ዳኛዎች
ለማስተካከልየፊፋ ዳኛዎች ኮሚቴ በጥር ፮ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ከ፵፫ አገራት የተውጣጡ ፳፭ የዳኛ ሦስትዮሾችን እና ፰ ረዳት ጥንዶችን (አራተኛና አምስተኛ ዳኛዎች) ለውድድሩ ሾሟል።[10][11]
የሽልማት ገንዘብ
ለማስተካከልፊፋ ለውድድሩ ያቀረበው ጠቅላላ የሽልማት ገንዘብ $576 ሚሊዮን ነው። ይህም ከ2010 እ.ኤ.አ. ውድድር ሽልማት ገንዘብ የ፴፯ ከመቶ ዕድገት አለው።[12] ከዚህ ውስጥ $70 ሚሊዮን የሚሆነው ተጫዋቾቹ ለሚጫወቱበት ክለቦች ተጫዋቾቹ ለሚደርስባቸው ጉዳት መካካሻ እንዲሆን ተሰጥቷል። ከውድድሩ በፊት እያንዳንዱ ቡድን ለዝግጅት ወጪው $1.5 ሚሊዮን የተረከበ ሲሆን ቀሪው ገንዘብ እንደሚመለከተው ተከፋፍሏል፦
- $8 ሚሊዮን - ለያንዳንዱ በምድብ ደረጃ የወደቀ ቡድን (፲፮ ቡድኖች)
- $9 ሚሊዮን - ለያንዳንዱ በየ፲፮ ዙር የወደቀ ቡድን (፰ ቡድኖች)
- $14 ሚሊዮን - ለያንዳንዱ በሩብ ፍፃሜ የወደቀ ቡድን (፬ ቡድኖች)
- $20 ሚሊዮን - በአራተኛ ደረጃ ለጨረሰው ቡድን
- $22 ሚሊዮን - በሶስተኛ ደረጃ ለጨረሰው ቡድን
- $25 ሚሊዮን - በሁለተኛ ደረጃ ለጨረሰው ቡድን
- $35 ሚሊዮን - ለአሸናፊው ቡድን
ከተማዎችና ስታዲየሞች
ለማስተካከልበአስራ ሁለት ከተማዎች የሚገኙ አስራ ሁለት ስታዲየሞች ለውድድሩ ተዘጋጅተዋል። ሰባቱ አዲስ የተገነቡ ሲሆን አምስቱ ደግሞ የተሻሻሉ ስታዲየሞች ናቸው።
መሰልጠኛ ሰፈሮች
ለማስተካከልእያንዳንዱ ቡድን የራሱ የሆነ የመሰልጠኛና መቆያ ሰፈር አለው። ፊፋ ፹፬ ዕጩ ከተማዎችን ካስታወቀ በኋላ[13] በጥር ፳፫ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. እያንዳንዱ የተሳታፊ ቡድኖች የመረጡትን ከተማ ይፋ አርጓል።[14]
የምድብ ደረጃ
ለማስተካከልምድብ ኤ
ለማስተካከልዋና መጣጥፍ፦ የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ኤ መለጠፊያ:የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ኤ
ምድብ ቢ
ለማስተካከልዋና መጣጥፍ፦ የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ቢ መለጠፊያ:የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ቢ
ምድብ ሲ
ለማስተካከልዋና መጣጥፍ፦ የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ሲ መለጠፊያ:የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ሲ
ምድብ ዲ
ለማስተካከልዋና መጣጥፍ፦ የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ዲ መለጠፊያ:የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ዲ
ምድብ ኢ
ለማስተካከልዋና መጣጥፍ፦ የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ኢ መለጠፊያ:የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ኢ
ምድብ ኤፍ
ለማስተካከልዋና መጣጥፍ፦ የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ኤፍ መለጠፊያ:የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ኤፍ
ምድብ ጂ
ለማስተካከልዋና መጣጥፍ፦ የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ጂ መለጠፊያ:የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ጂ
ምድብ ኤች
ለማስተካከልዋና መጣጥፍ፦ የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ኤች መለጠፊያ:የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ኤች
ማስታወሻ
ለማስተካከልማመዛገቢያ
ለማስተካከል- ^ (እንግሊዝኛ) "Pot allocations for the Preliminary Draw". FIFA.com (Fédération Internationale de Football Association) (27 July 2011). Archived from the original on 17 October 2013. በ27 July 2011 የተወሰደ.
- ^ (እንግሊዝኛ) "FIFA launch GLT tender for Brazil 2013/14". FIFA.com (Fédération Internationale de Football Association) (19 February 2013). Archived from the original on 22 October 2013. በ13 June 2014 የተወሰደ.
- ^ (እንግሊዝኛ) "If the World Cup started tomorrow". ESPN (12 June 2013).
- ^ (እንግሊዝኛ) "1 day to go". FIFA.com (Fédération Internationale de Football Association) (11 June 2014). Archived from the original on 15 July 2014. በ13 June 2014 የተወሰደ.
- ^ (እንግሊዝኛ) "Pot 1 seeds set for Brazil 2014 draws". FIFA.com (Fédération Internationale de Football Association). 17 October 2013. Archived from the original on 23 January 2015. https://web.archive.org/web/20150123150411/http://www.fifa.com/worldranking/news/newsid=2197884/index.html በ23 November 2013 የተቃኘ.
- ^ (እንግሊዝኛ) "Draw procedures approved". FIFA.com (Fédération Internationale de Football Association). 3 December 2013. Archived from the original on 8 July 2014. https://web.archive.org/web/20140708194238/http://www.fifa.com/worldcup/final-draw/news/newsid=2238498/index.html በ3 December 2013 የተቃኘ.
- ^ (እንግሊዝኛ) "Final draw procedures". FIFA.com (Fédération Internationale de Football Association) (3 December 2013). Archived from the original on 18 March 2019. በ3 December 2013 የተወሰደ.
- ^ (እንግሊዝኛ) "Final Draw reveals intriguing groups". FIFA.com (Fédération Internationale de Football Association). 6 December 2013. Archived from the original on 15 July 2014. https://web.archive.org/web/20140715174148/http://www.fifa.com/worldcup/news/y=2013/m=12/news=final-draw-reveals-intriguing-groups-2240026.html በ13 June 2014 የተቃኘ.
- ^ ሀ ለ (እንግሊዝኛ) "Regulations – FIFA World Cup Brazil 2014". FIFA.com (Fédération Internationale de Football Association). Archived from the original on 2014-03-08. በ2014-06-13 የተወሰደ.
- ^ (እንግሊዝኛ) "Referee trios and support duos appointed for 2014 FIFA World Cup". FIFA.com (Fédération Internationale de Football Association) (15 January 2014). Archived from the original on 12 July 2014. በ13 June 2014 የተወሰደ.
- ^ (እንግሊዝኛ) "Referees & assistant referees for the 2014 FIFA World Cup". FIFA.com (Fédération Internationale de Football Association). Archived from the original on 2014-05-28. በ2014-06-13 የተወሰደ.
- ^ (እንግሊዝኛ) "World Cup money pot increased to $576m". reuters.com. Archived from the original on 19 October 2015. በ25 April 2014 የተወሰደ.
- ^ (እንግሊዝኛ) "Team Base Camps Brochure". FIFA.com (Fédération Internationale de Football Association) (7 November 2013). Archived from the original on 6 June 2014. በ13 June 2014 የተወሰደ.
- ^ (እንግሊዝኛ) "Team Base Camps for Brazil 2014 announced". FIFA.com (Fédération Internationale de Football Association) (21 January 2014). Archived from the original on 8 July 2014. በ13 June 2014 የተወሰደ.