ኅዳር ፳፩
ኅዳር ፳፩ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፹፩ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፹፭ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፹፬ ቀናት ይቀራሉ።
ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች
ለማስተካከል፲፱፻፵፮ ዓ.ም. በኡጋንዳ የቡጋንዳ ንጉሥ ዳግማዊ ኤድዋርድ ሙቴሳ በአገሪቱ የብሪታንያ አስተዳደሪ ‘ሰር አንድሩው ኮሄን’ ተሽረው በስደት ወደለንደን ሄዱ።
፲፱፻፶፫ ዓ/ም ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በጋና፤ ላይቤሪያ፤ ቶጎ፤ ብራዚል ፤ ናይጄሪያ እና ካሜሩን የሚያካሂዱትን ጉብኝት ለመፈጸም ከአዲስ አበባተነሱ። ዳሩ ግን ዕቅዳቸውን ሳያጠናቅቁ በኢትዮጵያ የታኅሣሥ ግርግር መነሳት ምክንያት ጉዟቸውን አቋርጠው ይመለሳሉ።
፲፱፻፶፭ ዓ.ም. ዩ ታንት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በዋና ጸሐፊነት ተመረጡ። በዋና ጸሐፊነት ኮንጎ በአየር አደጋ የሞቱትን ዳግ ሃመርሾልድን ይተካሉ።
፲፱፻፶፱ ዓ.ም. የባርባዶስ ደሴት ከብሪታንያ ነጻነቷን ተቀዳጀች።
፲፱፻፷ ዓ.ም. የየመን ሕዝባዊ ሪፑብሊክ ከብሪታንያ ነጻነቷን ተቀዳጀች።
፲፱፻፷ ዓ.ም. በፓኪስታን በኋላ የአገሪቱ መሪ የሆኑት እና በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ወርደው በስቅለት ሞት የተቀጡት ዙልፊቃር አሊ ቡቶ የፓኪስታን ሕዝባዊ ፓርቲን መሠረቱ።
፲፱፻፷፯ ዓ/ም - በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የነዳጅ ክምችቱን ለማፈንዳት የተደረገው ሙከራ ከሽፏል
፲፱፻፺፰ ዓ.ም. በካምፓላ ኡጋንዳ የተወለዱት ጆን ታከር ሙጋቢ ሴንታሙ ዘጠና ሰባተኛው የዮርክ ሊቀ ጳጳስ ሆኑ። በዚህ ቤተ ክርስቲያን ይሄንን ታላቅ ሥልጣን የተቀበሉት የመጀመሪያው ጥቁር ጳጳስ ናቸው።
ልደት
ለማስተካከል፲፰፻፳፰ ዓ.ም. ሳሙኤል ላንግሆርን ክሌመንስ የተባለው አሜሪካዊ እና በብዕር ስሙ ማርክ ትዌይን የሚባለው ታዋቂ ደራሲ
፲፰፻፷፯ ዓ.ም. ታላቁ የሁለተኛው ዓለም ጦርነት መሪ እና የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዊንስተን ቸርቺል
ዕለተ ሞት
ለማስተካከልዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FO 371/154836 - Annual Report from Ethiopia for 1960
- {{en]] P.R.O., FCO 371/1829 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1974
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |