ህግ ተርጓሚ
ህግ ተርጓሚ ወይም ፍርድ ቤት፡ ፍርድ የመስጠት ስልጣን ያለው የመንግስት አካል ነው። ከሶስቱ ከፍተኛ የመንግስት አካላት ማለትም ህግ አውጭ፣ ህግ ተርጓሚ እና ህግ አስፈጻሚ አንዱ። ይህ አካል ህግ ተር ጓሚ የሚባለው ነው። የወንጀለኛ መቅጫ ህግ፣ ሲቪል ህግ፣ አስተዳደራዊ ህግ እና ሌሎች ህጎችን በየህግ የበላይነት ላይ መሰረት በማድረግ ይተረጉማል።
ታሪክ
ለማስተካከልፍርድ በኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ታሪክ ያለው ክንውን ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ በተለምዶ ወይም ባህል በበላ ልበልሃ እየታገዘ በመንደር ሽማግሌዎች ወይም በሀገረ ገዥዎች ፊት ይቀርብ ነበር። ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አገዛዝ ወዲህ በዘመናዊው የመንግስት መዋቅር የህግ ተርጓሚነትን የመንግስት ሰልጣን ተሰጥቶት መንግስት በሾማቸው ዳኞች ይመራል።
ገለልተኝነት
ለማስተካከልይህ አካል በዘመናዊዉ የዴሞክራሲ መርህ ከየትኞቹም የመንግስት አካላት በገለልተኝነት ይንቀሳቀሳል። ሶስቱም የመንግስት አካላት ጣልቃ መግባት አይችሉም። በሃገሪቱ የሚገን ማንኛውም ዜጋ፣ አካል፣ ወይንም ተቋም ይዳኝበታል።