ሰኔ ፮
ሰኔ ፮ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፸፮ኛው ቀን ሲሆን የፀደይ (በልግ)ወቅት ፸፩ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፺ ቀናት፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፹፱ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፰፻፳፪ ዓ/ም - ፴፬ ሺ የፈረንሳይ የወረራ ሠራዊት ከዛሬይቱ አልጄርስ በስተምዕራብ በምትገኘው ‘ሲዲ ፈሩሽ’ በተባለ ወደብ ላይ አርፈው አልጄሪያን በቅኝ ግዞት ያዙ።
- ፲፱፻፳፮ ዓ/ም - የናዚያዊ ጀርመን መሪ አዶልፍ ሂትለር እና የፋሺስታዊ ኢጣልያ መሪ ቤኒቶ ሙሶሊኒ በኢጣልያን ከተማ ቬኒስ ላይ ተገናኙ። ከግንኝነታቸው በኋላ ሙሶሊኒ በሂትለር ላይ በማሾፍ “ኮስማና ሞኝ ጦጣ” ብሎታል። (“ጀበናዋ ድስትን ሻንቅላ ብላ ሰደበች” እንደሚሉ!)
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ከሰኔ ፮ - ፲፯ የተካሄደው ሁለተኛው የነፃ አፍሪቃ አገሮች ስብሰባ አዲስ አበባ ላይ ሲከፈት ከሁለት መቶ ሃምሣ በላይ ልዑካን እና ተመልካቾች ተሳትፈዋል።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የንግድ ሚኒስትር አቶከተማ ይፍሩ የተመራ የሰባት ኢትዮጵያውያን ልዑክ ለአሥራ ሁለት ቀን የንግድ ውይይት ወደቻይና መዲና ቤይጂንግ አመራ።
- ፲፱፻፺፪ ዓ/ም - የኢጣልያ መንግሥት ግንቦት ፭ ቀን ፲፱፻፸፫ ዓ/ም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንን ጳጳስ ዳግማዊ ዮሐንስ-ጳውሎስን በጥይት ያቆሰለውን ቱርክ፣ ሜህመት አሊ አጅካን (Mehmet Ali Agca) በምኅረት ከእስር ለቀቀው።
ልደት
ለማስተካከል- ፲፱፻፴፮ ዓ/ም - የደቡብ ኮሪያ ተወላጅ የሆኑት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ባን ኪ ሙን በዚህ ዕለት ተወለዱ።
ዕለተ ሞት
ለማስተካከልዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል- (እንግሊዝኛ) http://en.wikipedia.org/wiki/June_13
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FO 371/154836 - Annual Report from Ethiopia for 1960
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1660 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1973
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |