ጥቅምት ፲፭
(ከጥቅምት 15 የተዛወረ)
ጥቅምት ፲፭ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፵፭ኛው እና የመፀው ፳ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፪፻፳፩ ቀናት ሲቀሩ፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፳ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፱፻፶፭ ዓ/ም - በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአሜሪካ ዋና ተወካይ አድላይ ስቲቨንሰን፣ የሶቪዬት ሕብረት በኩባ ደሴት ላይ የኑክልዬር መሣሪያዎችን ማስቀመጧን የሚያሳዩ ከአየር የተነሱ ማስረጃ ምስሎችን ለጸጥታ ጉባዔው አቀረቡ።
- ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - በአፍሪቃ ከብሪታንያ ነጻነቷን በመቀዳጀት ዘጠነኛዋ አገር፣ የቀድሞዋ የሰሜን ሮዴዥያ፤ አዲሷ ዛምቢያ ኬኔዝ ካውንዳን የመጀመሪያው ፕሬዚደንት አድርጋ መረጠች።
- ፲፱፻፷፬ ዓ/ም - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተ.መ.ድ.) ታይዋንን ከአባልነት አስወጥቶ የቻይና ሕዝባዊ ሪፑብሊክን በአባልነት እንድትገባ የሚያስችለውን ድንጋጌ በሁለት ሦስተኛ ድምጽ አጸደቀ።
ልደታት
ለማስተካከልዕለተ ሞት
ለማስተካከል- ፲፰፻፶፱ ዓ/ም - የምስር ተወላጁ፣ ዓፄ ቴዎድሮስን ቅብዐ-መንግሥት ቀብተው ያነገሡት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት፣ አቡነ ሰላማ በቁም እስር ላይ በንበሩበት በመቅደላ ምሽግ ውስጥ በዚህ ዕለት አርፈው፤ እዚያው መቅደላ መድሃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ተቀበሩ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - ስመጥሩው ኢትዮጵያዊ የማራቶን ጀግና አበበ ቢቂላ አረፈ። አበበ በ፲፱፻፶፪ ዓ.ም በሮማ የኦሊምፒክ ውድድርና በ፲፱፻፶፮ በቶክዮ የኦሊምፒክ ውድድር አሸናፊ ሲሆን በኦሊምፒክ ውድድር የወርቅ ሽልማት በማግኘት የመጀመሪያው የሰሃራ በታች አፍሪቃዊ ነው።
ዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FO 371/154836 - Annual Report from Ethiopia for 1960
- (እንግሊዝኛ) http://news.bbc.co.uk/onthisday/hi/dates/stories/october/25 Archived ማርች 12, 2007 at the Wayback Machine
- (እንግሊዝኛ) http://www.nytimes.com/learning/general/onthisday/20081025.html
- (እንግሊዝኛ) Marsden, Philip; The Barefoot Emperor; HarperPerennial (2007)
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |