ኅዳር ፴
ኅዳር ፴ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፺ኛው ቀን እና የወሩ መጨረሻ ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፸፮ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፸፭ ቀናት ይቀራሉ።
ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች
ለማስተካከል፲፰፻፴፭ ዓ/ም በአንኮበር እና ዙሪያዋ የተከሰተው የመሬት እንቅጥቅጥ ከተማዋን አወደማት።
፲፰፻፸፭ ዓ/ም በሉዊዚያና ግዛት ‘ ፒ. ቢ. ኤስ. ፒንችባክ’ የመጀመሪያው ጥቁር አሜሪካዊ ገዥ ሆነ ።
፲፰፻፺፰ ዓ/ም በፈረንሳይ መንግሥትን እና ቤተ ክርስቲያንን የሚለየው ህግ ጸደቀ።
፲፱፻፶፬ ዓ/ም የቀድሞዋ ታንጋኒካ ከብሪታንያ ነጻነቷን ተቀዳጀች። ከነጻነት በኋላ በዚሁ ዕለት በ፲፱፻፶፯ ዓ/ም ታንጋኒካ ከዛንዚባር ጋር ተዋሕዳ የዛሬይቱን የታንዛኒያ ሪፑብሊክ መሠረቱ።
፲፱፻፹፫ ዓ/ም በፖሎኝ አገር ሌክ ቫሌሳ የመጀመሪያው በሕዝብ የተመረጠ ፕሬዚደንት ሆነ ።
፳፻፩ ዓ/ም በአሜሪካ የኢሊኖይ ገዥ ሮድ ብላጎዬቪች በብዙ ወንጀሎች ተከሶ በፌዴራል ህግ አስከባሪዎች ተያዘ። ፈጽሟል ከተባሉት ወንጀሎች አንዱ በፕሬዚደንትነት የተመረጡትን የባራክ ኦባማን የእንደራሴዎች ምክር ቤት (United States Senate) አባልነት በገንዘብ ሊሸጥ ሞክሯል በመባል ነው ።
ልደት
ለማስተካከልዕለተ ሞት
ለማስተካከል፲፰፻፵፰ ዓ/ም የሸዋው ንጉሥ እና የዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ አባት ንጉሥ ኃይለ መለኮት በኃይል ሊያስገብሯቸው ከመጡት ከዓፄ ቴዎድሮስ ጋር ለጦርነት ሲዘጋጁ በድንገት ታመው አረፉ።
ዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል- (እንግሊዝኛ) Gouin Pierre, EARTHQUAKE HISTORY of ETHIOPIA and the HORN OF AFRICA, IDRC publication, p34, Ottawa, Ont.,(1979)
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |